
ሠላም ለሁሉም ነገር መሠረት ነው፡፡ ወጥቶ ለመግባት፣አርሶ ለመብላት፣ወልዶ ለመሳም፣ተምሮ ለመጨረስ፣ተኝቶ ለመታከም በአጠቃላይ ለሰዉ ልጆች ብቻ ሳይሆን ህይወት ላለዉ ነገር ሁሉ ሰላም ወሳኝ መሣሪያ ነዉ።ሠላም በእጃችን ያለ ትልቅ ዉድ ሃብት ነዉ።የቀዬዉ ሰዉ ጧት ማልዶ ለጉዳዩ ሲወጣ
“አቤቱ በሠላም አዉለኝ”የሚለዉ የሠላምን ዋጋ ጠንቅቆ ስለሚረዳ ነዉ። በሠላም ወጥቶ መመለስ ምኑን ያህል ጣፋጭ እንደሆነ ስለሚረዳ ነዉ።ሠላም የትም ያለ፣ከሌላ ቦታ የሚገኝ ሳይሆን፤ከእኛዉ የሚመነጭ፤እኛ ጋር ያለ ጉዳይ ነዉ። መንግሥት በሀገሪቱ የሚከሰቱ የፀጥታ ቸግሮችን በመፍታት ሠላምን ለማስፈን የተለያዩ አማራጮችን ሲጠቀም ቆይቷል፡፡ በክልላችን ይህ መንገድ በመጠቀም ብዙ ተግባራት ተከናዉኗል።
በዚህም በተለያዩ ጊዜ በተፈጠረው የሠላም ኮንፍራንሶችና ውይይቶች በክልሉ አካባቢዎች ሠላም መስፈን ችሏል፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበች ክልልም ክልሉ ከተመሰረተ ባለፉት ሁለት ዓመት ወዲህ ቀደም ሲል የህዝቦች ትልቅ ጥያቄ የነበረው በየአከባቢው በሠላም እጦት ምክንያት የሚፈጠረው ግጭት፣እርስበርስ ግድያ፣ ዘረፋና መፈናቀል በማስቀረት ሠላምን ለማረጋገጥ የክልሉ መንግስት እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በጋራ አቅዶ ሲሰራ ከርመዋል።
አቶ አንድነት አሸናፊ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ኃላፊ ናቸው፡፡ እንደ አቶ አንድነት አሸናፊ ገለፃ ከክልልና ከታችኛው ፀጥታ ሀይሎች እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ሠላም የማስፈን ስራም በሰፊው መሠራቱን ተናግረዋል ።
ባለፉት ጊዜያት በተከሰቱ ግጭቶች በህዝቦች መካከል የነበሩ መከፋፈል፣ቅሬታና አለመተማመን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታታት፣ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስ፣ጫካ የነበሩ ታጣቂ ሽፍታዎች ወደ ሠላማዊ ኑሮ እንዲመለሱ ማድረግና ወንጀለኞች ላይ ህግ የማስከበር ስራ መከናወኑን ገልፀዋል፡፡
በዚህም በቤንች ሸኮ ዞን በደቡብ ቤንች፣ጉራፈርዳ፣ሸኮ ወረዳዊች በሸካ ዞን በቴፒ ከተማና በየኪ ወረዳ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት ከሀገር ሽማግሌዎች፣ከሀይማኖት አባቶችና ከሌሎች ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እንዲሁም ከአመራሮች ጋር በጋራ በመቀናጀት ባህላዊ እርቅ በማውረድ ተለያይተው የነበሩን በማስታረቅ፣የተጎዱትን እርስበእርስ እንዲካካሱና እንዲጠያየቁ የማድረግ ተግባር መፈጸሙን አቶ አንድነት አሸናፊ ተናግረዋል።
አሁን ላይ በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች ተፈናቀለው የነበሩ ማህበረሰቦች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ያሉት አቶ አንድነት መሬት የተነጠቀባቸው እንዲመለስላቸው፣የቤት ውድመት የደረሰባቸው በትብብር እንዲሰራ እንዲሁም መልሶ ማቋቋምና ማደራጀት ስራዎች እንደተሰሩም አንስተዋል።
በምዕራብ ኦሞ ዞን የአርብቶ አደር አከባቢ በዞኑ ባሉት ወረዳዎችና ቀበሌዎች በነበሩ ፀጥታ ችግር ምክንያት መንግስታዊ አገልግሎቶች ተቋርጠው እንደነበሩ አስታውሰው በ2014 ዓ.ም እና በ2015 ዓ.ም ከህዝቡ ጋር በተደረገው ውይይቶችና ንቅናቄዎች አገልግሎት እንዲጀመርና ሠላም እንዲሰፍን ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውንም አብራርተዋል።
በዞኑ ቤሮ፣ ሱርማና በማጂ ወረዳዎች ስለሠላም አስፈላጊነት ከህዝቡ ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ የተፈጠሩ ችግሮችን የማስተካከል ስራ በመስራቱ የነበሩ ችግሮች ሊቀንሱ እንደተቻሉና ከመንግሥት ግምጃ ቤት የተዘረፉ መሳሪያዎችን የማስመለስ ስራ መሰራቱንም ለአብነት ጠቅሰዋል።
ክልሉ የግብርና ኢንቨስትመንት፣ማዕድን ምርትና የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን የያዘ አካባቢ በመሆኑ ልማቱን ለማረጋገጥ ለሰላም ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል ።
በክልሉ ቀደም ሲል በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፈርዳ፣በሸኮ፣ በሸካና በምዕራብ ኦሞ ዞኖች በፀጥታ ችግር ምክንያት የተለያዩ ፕሮጀክቶች ቆሞ እንደነበሩ የጠቀሱት ኃላፊው ክልሉ እንደክልል ተደራጅቶ ስራ ከጀመረ ወዲህ በመጣው አንፃራዊ ሠላም እነዚህም ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል ነው ያሉት።
ከዚህም ባሻገር የኢንቨስትመንት ፍስት እንዲጨምር ፣የቆሙ መሠረተ ልማት ስራዎች ወደ ተግባር እንዲገቡ፣በከተማና በገጠር የተቀዛቀዘ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሳለጡ ተደርጓል ሲሉም ተናግረዋል ።
የመጣውን ሠላም ለማጽናት የፀጥታ ኃይል አደረጃጀቶችን በማጠናከር፣በየደረጃው የሚገኙ አካላትን ያሳተፈ የሠላም ኮሚቴ፣የሠላም ምክር ቤት ፣የማህበረሰብ ደህንነት ፓትሮልና ገለልተኛ የሠላም አማካሪ ምክር ቤት የማቋቋም ስራ በስፋት መሰራታቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።
በታችኛው መዋቅር የሚልሻ አባላትን ማጥራት፣ ማሰልጠን እንዲሁም መልሶ የማደራጀት ስራ በልዩ ትኩረት እንደተሰራም አብራርተዋል።
ከመንግሥት እና ከፓርቲ ለሠላም ከተሰጠው ትኩረት አኳያ በየደረጃው ላሉት ማህበረሰብ ክፍሎች ግንዛቤ ማስጨበጫ እና የመጣውን ሠላም ለማጽናት የክልሉ አድማ ብተና፣ከፍተኛ አመራሮች፣ተቋማት ጥበቃ ኃይሎችን መልሶ ማደራጀት፣ትጥቅ ማጠናከር እንዲሁም የስጋት ቀጠናዎች ኃይሎችን በማሰማራት ችግሩ እንዳይከሰት ቀድሞ የመከላከል ስራ ላይ ከወትሮ በተለየ ዝግጁነት እንዲጠናክር መደረጉን ተናግረዋል።
ሠላምን ለማረጋገጥ የተቀላጠፈ የመረጃ ልውውጥ መንገዱ ወሳኝ በመሆኑ በየቀበሌው ከፀጥታ መዋቅር ውጭ የሆኑ አካላት በመመልመል ስጋት የሚጭሩ አካላትን ለፀጥታ አካላት ፈጥኖ እንዲያደርሱና የመረጃ ልውውጡን በቴክኖሎጅ በማስታገዝ የግንኙነት አድማስ ለማስፋት የአሰራር ስርዓት የመዘርጋት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።
ዛሬም ቢሆን በክልላችን በአርብቶ አደር አከባቢዎች አሁንም ጠንካራ ስራ የሚፈልጉ ብዙ ያልተሻገርናቸው ጉዳዮች ስላሉ በትኩረት ይሰራል ብለዋል ኃላፊው።
በአጎራባች አከባቢዎች አልፎ አልፎ የሚስተዋለው የህገወጥ የጦር መሳሪያ፣ወሰንና መሠል ጉዳዮች ለማስቀረት ከጋምቤላ ክልል ጋር በህግ ማዕቀፍ የሚመራ የሠላምና የልማት የጋራ ፎረም ሰነድ መፈራረሙንም አስታውቀዋል።
የውስጣችን ሠላም ወደላቀ ደረጃ በማሸጋገር አሁን የመጣውን አንፃራዊ ሠላም አስተማማኝ ለማድረግ በየደረጃው ካሉት ከፀጥታ መዋቅር ጋር በቅንጅትና በትብብር ይሰራል ያሉት አቶ አንድነት አሸናፊ በክልሉ በተመዘገበውና በመጣው የሠላሙ ውጤት የህዝቡ ሚና ከፍተኛ እንደነበርም አስረድተዋል።
አቶ አንድነት የመጣው ሠላም ወደ ኋላ እንዳይመለስ ህዝቡ የተለመደውን ያለሰለሰ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥር አቅርበው ህዝቡም ይህን እንደሚያደርግ ሙሉ እምነትና ተስፋ አለኝ ስሉ አክለዋል።
ያለሰላም መረጋገጥ ኢኮኖሚና ማህበራዊ መስተጋብሮችን ማሳከት ስለማይቻል ሁሉም በባለቤትነት ለሰላም ዘብ እንዲቆም ጥሪያቸውን ያቀረቡት አቶ አንድነት በክልሉ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን ማስቆምና አዲስ ግጭት እንዳይከሰት ጭምር ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ሰላም ከለለ ወቶ ማደር አይቻልም። ሰላም ለአንድ ሀገር ዕድገት መሠረት ነዉ።
it’s not limited. For more contact the HRM