የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የዉክልና ሥራ የማጠቃለያ መድረክ በቦንጋ እየተካሄደ ነው

Spread the love

የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የዉክልና ሥራ የማጠቃለያ መድረክ በቦንጋ እየተካሄደ ነው

የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በክልሉ ከወከላቸው ህዝቦች ጋር ያደረጉትን ውይይትና የመስክ ምልከታን በማስመልከት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ የተከበሩበአቶ ወንድሙ ኩርታ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት የህዝብ ተወካይ ምክር ቤት አባላት ከመረጧቸዉ ህዝቦች ጋር ዉይይት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

ዛሬ በሚቀርበዉ ግብረ መልስ ከአስፈጻሚ አካላት ጋር ዉይይት የሚደረግ ሲሆን በክልሉ በፌደራል መንግስት የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ላይ ከምክር ቤት አባላቱ ጋር ምክክር እንደሚደረግ ጠቅሰዋል።

በዚህም በመስክ ምልከታ ሪፖርት እየቀረበ ሲሆን በቀረበው የመስክ ሪፖርት መነሻ በማድረግ በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት የሚደረግም ይሆናል።

በመድረኩም የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉን ጨምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ፣የክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎችና የክልሉ መንግስት አስፈፃሚ አካላት እየተሳተፉ ነው።

በተከተል ወ/ሚካኤል

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *