የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ፖሊስ የማርሽ ባንድ ምልምል ሰልጣኞች ስልጠናቸውን ጀመሩ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ፖሊስ የማርሽ ባንድ ምልምል ሰልጣኞች ስልጠናቸውን ጀመሩ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያቋቁመውን የፖሊስ ማርሽ ባንድ አባላትን ለማደራጀት ከሁሉም የክልሉ ዞኖች የተመለመሉ ወጣቶች ወደ ስልጠና ገብተዋል።

ሰልጣኞቹ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አቦስቶ ካምፓስ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፣ ስልጠናቸውንም በላቀ የፖሊሳዊ ሥነ-ምግባር እንዲከታተሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

በአቀባበል ሥነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሰው ኃይል ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር ሀብታሙ መላኩ፣ ኮሚሽኑ የፖሊስ ተቋሙን በሰለጠነና በዘመነ የሰው ኃይል ለማጠናከር በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

“የማርሽ ባንድ ማቋቋም የዚሁ ትልቅ ዕቅድ አካል ነው” ያሉት ረዳት ኮሚሽነሩ፣ የኮሚሽኑ ማኔጅመንት ለክልሉ መንግሥት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶና በጀት ተመድቦለት ከየዞኖቹ 100 ወጣቶችን በመመልመል ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል ማስገባት መቻሉን አስረድተዋል።

ሰልጣኞቹ በቅድሚያ መሰረታዊ የፖሊስ ስልጠና እንደሚወስዱ የገለጹት ረዳት ኮሚሽነር ሀብታሙ፣ “ይህ ስልጠና ለቀጣዩ የሙዚቃ (ማርሽ ባንድ) ስልጠና መሰረት የሚጥል በመሆኑ በከፍተኛ ዲስፕሊንና ዝግጁነት መከታተል ይገባችኋል” ሲሉ አሳስበዋል።

የአቦስቶ ካምፓስ ዲን ተወካይ ዋና ኢንስፔክተር ታምራት በየነ በበኩላቸው፣ ሰልጣኞቹን “ውድ ህይወቱን እየገበረ የሀገርን ሰላም ወደሚያሰፍነው ክቡር የፖሊስ ሙያ እንኳን በደህና መጣችሁ” በማለት ተቀብለዋቸዋል።

ካምፓሱ ከተለያዩ ክልሎች ለሚመጡ የፖሊስ አመራሮችና አባላት ስልጠና በመስጠት ሀገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ኢንስፔክተሩ፣ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ምልምሎችም የተሟላ ስልጠና ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አረጋግጠዋል።

በስልጠናው ወቅት ሰልጣኞች ጋር በመሆን የመስክና የክፍል ውስጥ ትምህርቶችን እንደሚከታተሉ የተገለጸ ሲሆን፣ በአካል ብቃት የዳበረና በሥነ-ምግባር የታነጸ የፖሊስ ቁመና እንዲኖራቸው ትኩረት እንደሚሰጥ የአቦስቶ ካምፓስ የፖሊሳዊ ስልቶችና አካል ብቃት ስልጠና ክፍል ኃላፊ ተወካይ ኢንስፔክተር እሰይ አጥናፋ ተናግረዋል። “እናንተ የክልላችሁ አምባሳደሮች ናችሁ” ያሉት ኢንስፔክተሩ፣ ሰልጣኞቹ በቆይታቸው ሊከተሏቸው የሚገቡ ደንቦችንና ሥርዓቶችን በዝርዝር አብራርተዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ፣ ይህ ፕሮግራም 100 ወጣቶች የስራ ዕድል እንዲያገኙ ማድረጉን ጠቅሰው፣ ሰልጣኞቹ በቁርጠኝነት እንዲሰለጥኑ ካሳሰቡ በኋላ ለአቦስቶ ካምፓስ አመራሮች ላደረጉት አቀባበል በኮሚሽኑ ስም ምስጋና ማቅረባቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብና ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *