የትግራይ ክልል ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄዱ
የትግራይ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የተሰሩ ስራዎች የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።




የልምድ ልዉዉጡ ዓላማ በምርምር ማዕከል የተከናወኑ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን በመጎብኘት ለቀጣይ ስራዎች የጋራ የስራ ትብብርን ለማጠንከር ያለመ ነው።
በጉብኝቱ መርሃ ግብር ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል አለሙ፤የትግራይ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ኃላፊዎችና የማናጅመንት አባላት በክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የተሰሩ የመደበኛ እና የፕሮራም ስራዎች መሰረት ያደረገ የልምድ ልውውጥና የእውቀት ሽግግር ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ በምርምር የተደገፉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን የማላመድና ማፍለቅ ስራ በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን አቶ አማኑኤል ገልጸዋል ።
የምርምር ስራ በአንድ ክልል ብቻ የሚታጠር አይደለም ያሉት አቶ አማኑኤል በሀገር ውስጥ ያሉ የምርምር ተቋማት በጋራ ተቀናጅተው ሲሰሩ አሁን እየተስተዋለ ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ ሊቋቋም የሚችል ዝሪያ በጋራ የማፍለቅ፣የማዳስ ስራ በጋራ ሲሰራ የተጠናከረ የቴክኖሎጂ የማመንጨት አቅም እንደሚኖር ጠቁመዋል፡፡
ከዚህም ባለፈ በሀገር አቀፍ ደረጀ ተወዳዳሪነትን የሚያሰፉ በግብርና የቴክኖሎጂዎችን በጋራ የማፍለቅ፣ እውቀት የመቀያየር እና በሰው ሃይል የመደጋገፍ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች ያሉትን ውጤታማ የሆኑትን የቴክኖሎጂዎችን ለመቀያየር እንደዚህ አይነት ከክል ክልል የሚደረጉ የልምድ ልውውጥ ሰፊ እድል የሚፈጥር መሆኑን አንስተዋል።
የትግራይ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ገ/አምላክ በዛብህ፤ በቦንጋ ምርምር ማዕከል የተከናወኑ ያሉ የምርምር ስራዎች ላይ የልምድ ልውውጥ ለማድረግና ለቀጣይ ስራዎች የጋራ ትብብርን ለማጠንከር ያለመ መሆኑን ተናግረዋል ።
ሁለቱ የምርምር ኢንስቲትዩቶች የተለያዩ የምርም ስራዎች የሚያከናውኑ መሆኑን አንስተው የትግራይ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሚያከናውናቸውን የምርምር ውጤቶች በቦንጋ ግብርና ምርምር ማዕከል ገለፀ ማድረጋቸውንና በቀጣይ በምርምር ስራዎች ላይ ለመተጋገዝና በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉን ዶክተር ገ/አምላክ ገልፀዋል፡፡
የቦንጋ ግብርና ምርምር ማዕከል በእንስሳት፣ በአዝርዕት ሰብሎች እና በተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ እያከናወነ ያለው የምርምር ስራዎች ውጤታማና ለትግራይ ክልል ምርጥ ተሞክሮ የሚሆን እንደሆነም ጠቁመው በምርምር ማዕከሉ የተጀመሩ ውጤታማ ተግባራት ሊጠናከሩ ይገባልም ብለዋል፡፡
ጉብኝቱ በቦንጋ ግብርና ምርምር ማዕከል እየተከናወኑ ያሉ በቴክኖሎጂ የታገዙ የተለያዩ የምርምር ስራዎች እና የውሽውሽ ሻይ ልማት ስራዎች ጉብኝት ተደርጓባቸዋል ።
በተከተል ወ/ሚካኤል
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
