የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፡-

Spread the love

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፡-

“በቬይትናም የቶዮ የፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫ ፋብሪካ በነበረን ጉብኝት እና ከኩባንያው ፕሬዝደንቱ ጋር በነበረን ውይይት የፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫዎችን በሀገራችን ለማምረት ተስማምተን ነበር። ዛሬ በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ በነበረን ጉብኝት በፓርኩ ከፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጪያዎችን እያመረቱ በመመልከታችን ደስታ ተሰምቶናል። ማምረቻው በከፍተኛ ጥራት ከፍተኛ ምርት የማምረት አቅም የተላበሰና በዘመናዊ የማሽን ሥርዓት የሚሰራ ሲሆን የምርት ውጤቱ ለማኑፋክቸሪንግ የውጪ ንግድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል። ሁለት ተጨማሪ ማምረቻዎች በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ሲሆን ወደ ምርት የገባውን ማምረቻ ሥራ ሂደት ተመልክተናል። ይኽ ሥራ እሴት የተጨመረባቸው እና ያስቀመጥናቸውን ግቦች እና ፖሊሲዎች የሚያሳኩ ጨዋታ ቀያሪ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት ከሚያደርገው የኢንቨስትመንት ስትራቴጂያችን ጋር የተጣጣመ ነው።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *