ወጣቶች የሀገራቸውን የወደፊት ዕጣ ፋንታ የማሳመር ሂደት ላይ ሊሳተፉ ይገባል ተባለ

Spread the love

ወጣቶች የሀገራቸውን የወደፊት ዕጣ ፋንታ የማሳመር ሂደት ላይ ሊሳተፉ ይገባል ተባለ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ወጣቶች ሀገሪቱ ያለፈችባቸውን መንገዶች የማስተካከል ብቻ ሳይሆን መጪውን እጣ ፋንታዋን የማሳመር ሂደት ላይ ንቁ ተሳታፊ ሊሆኑ ይገባል አለ።

ምክክር ኮሚሽኑ ‘የወጣቶች ሚና ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር’ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከአማራ ክልል ወጣቶች ጋር የሚያካሂደውን ውይይት የመጀመሪያው ምዕራፍ ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ ጀምሯል።

በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ብሌን ገብረ መድኅን እንዳሉት፤ ወጣቶች ኢትዮጵያ ያለፈችባቸውን መንገዶች የማስተካከል እና መጪውን እጣ ፋንታዋን የማሳመር ሂደት ላይ በንቃት መሳተፍ አለባቸው።

ከአሁን በፊት በነበሩ የምክክር ኮሚሽኑ ሂደቶች ወጣቶችን እንደ አንድ የማኅበረሰብ ክፍል መሳተፋቸውን አስታውሰዋል።

ይህንን ተሳትፎ ለማጠናከርም የተለያዩ የሃሳብ ግብአቶችን ለማግኘት ከተለያዩ ሙያዎች የተውጣጡ ወጣቶችን ማሳተፍ ማስፈለጉንም ተናግረዋል።

ከአማራ ክልል ወጣቶች ጋር የሚያካሂደው የመጀመሪያ ምዕራፍ ውይይት ለአራት ቀናት ይቆያል።

በመድረኩም በሀገራዊ ምክክር ሂደት የወጣቶች ተሳትፎና ሚና፣ በምክክሩ ሂደት የወጣቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎና አካታችነት እንዲጎለብት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሚና ተግባራት እና ሌሎች ሃሳቦች ላይ ውይይት ይደረጋል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *