በአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ለአህጉራዊ ለውጥ እና ለዜጎች ተጠቃሚነት በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል፦ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)

በ12ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ለአህጉራዊ ለውጥ፣ ለዜጎች ተጠቃሚነት እና ለአገረ መንግሥት ግንባታ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱን የብልጽግና ፓርቲ ዓለም አቀፍና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በጋና አክራ “ከፖለቲካ እስከ ብልፅግና” በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደውን 12ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ አስመልክቶ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
በጉባኤው በአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ትብብርን ለማጠናከርና ለአህጉራዊ እድገት ተስፋ የሚሆን የፓርቲዎች ጥምረትን እውን ለማድረግ ያለመ ውይይት መካሄዱን ተናግረዋል፡፡
ጉባኤው የፖለቲካ ፓርቲዎች የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ፓርቲዎች ኢኮኖሚያዊ ሽግግርን፣ የዘላቂ ሰላም ግንባታ እና የአገረ መንግስት ግንባታን ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት እንዳለባቸውም መግባባት ላይ መደረሱን ነው ያብራሩት፡፡
ይህም ጠንካራ አፍሪካን ለመገንባት ትልቅ መሠረት የሚጥል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የአፍሪካ ፖለቲካን ካለመተማመንና የጥርጣሬ አካሄድ በማውጣት በጋራ አህጉራዊ አጀንዳዎች ላይ አሻራን ለማኖር የሚያስችል ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፤ የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገራዊና አህጉራዊ ሁለንተናዊ ዕድገት ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው መግለጻቸውንም አንስተዋል።
ፓርቲዎች በተናጠል ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ባሻገር መተማመን፣ መተባበር እና ለጋራ ዓላማ መግባባት ፈጥረው መንቀሳቀስ እንደሚገባቸውም እንዲሁ፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች ለጠንካራ አገርና አህጉር ግንባታ፣ ለአገረ መንግስት ቅቡልነት እና ለተረጋጋና ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ባህል ግንባታ ትልቅ ትኩረት በመስጠት መስራት እንዳለባቸው መግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል፡፡
ፓርቲዎች ውስጣዊ ሪፎርም በማድረግ ለአዎንታዊ እና ዘላቂ ሰላም ግንባታ አሻራቸውን ማኖር እንዳለባቸውም መግባባት ላይ መደረሱን ጠቁመዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን


በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

በትዊተር twitter.com/sweprs

በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

በሊንክደን
https://www.linkedin.com/company/southwest-communications/
