ከአጋር ሀገራት እና ድርጅቶች የተገኘውን ሀብት በቀጥታ ወደ ማህረበረሰቡ እንዲወርድ መስራት እንደሚያስፈል ተገለፀ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያዊ ህዝቦች ክልል ደን፣ አከባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ የ REDD+ እስትሪንግ ኮሚቴ የ2017 ዕቅድ አፈጻጸምና የ2018 ዕቅድ በቦንጋ ከተማ ገምግሟል።




በግምገማው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኢንጂነር አስራት ገ/ማርያም የአየር ንብረት ለውጡን መቋቋም የሚችል ኢኮኖሚ ለመገንባት እየተሰራ ያለውን ስራ የሚደግፉ አጋር ድርጅቶችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ልንጠቀም ይገባል ብለዋል።
ከዚህ ቀደም በደንና አካባቢ ጥበቃ ላይ ይሰሩ የነበሩ REDD+ እና CRFL የተሰኙ አጋር ድርጅቶች ተዋህደው ወደ ተግባር መግባታቸውን የገለፁት ኢንጂነር አስራት(ዶ/ር) ለደን መጨፍጨፍ መንስኤ የነበረውን የማህረሰብ ኑሮ ለማሻሻል ከፕሮጀክቶችና አጋር ሀገራት የተገኘውን ፈንድ ለታለመለት ዓላማ ለማዋል የእስትሪንግ ኮሚቴው ድጋፍና ክትትል ወሳኝ መሆኑን አውስተዋል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የክልሉ የርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ አቶ ንጉሠ ወ/ጊዮርጊስ የኮሚቴ አባላት የፕሮጀክቱ አፈጻጸም ችግር ፈቺና የዘርፉ ቀጥተኛ ተዋንያን ወደ ሆኑት ህብረተሰብ ክፍል በትክክል መድረሱን የመከታተል ኃላፊነትን እንዲወጡ አሳስበዋል።
ፕሮጀክቶችን ከቢሮዎች ጋር እንዲሁም ከምርምር ተቋማት ጋር በማቀናጀት በጀትን በወቅቱ ወደ ስራ ማዋል ያስፈልጋል ያሉት አቶ ንጉሠ በበጀት አደላደል ጊዜ የሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚነት ላይ ልዩ ትኩረት እንዲደረግ አስገንዝበዋል።
የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን በዝርዝር ያቀረቡት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር ዬርቾ ብርሃኑ በበኩላቸው REDD+ በ2017 በጀት ዓመት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከወኑን ጠቅሰው ለአብነትም በደን ዙሪያ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ ታቅደው ከ 3 ሺ 3 መቶ በላይ ለሚሆኑት በዶሮ፣ በበግ ዘረመል ማሻሻያ፣ እንሰትና ሶላር አቅርቦት ሥራ ተሰርቷል ብለዋል።
ፕሮጀክቱ ሀገራዊ አቅጣጫን መሠረት በማድረግ ችግኝ ጣቢያዎችን በማስፋት ሀገር በቀል ዛፍፎችን በመትከል ለአረንጓዴ አሻራ የበኩሉን ሚና እንደተወጣ አመላክቷል።
አሳታፊ የደን አስተዳደርን በማጠናከር እንድሁም ሴቶች፣ ወጣቶችና ልዩ ድጋፍ የሚሹ ህብረተሰብ ክፍሉን ለመደገፍ ከበጀቱ 9 % በላይ ማቅረቡ ተገልፀው በዝህም ለተለያዩ ማህበራት በሁሉም ዞኖች ማድረስ መቻሉም ተብራርተዋል።
በቀጣይ ሁለቱ ፕሮግራሞችን በማቀናጀት ከየዘርፉ የተቀመሩ መልካም ተሞክሮዎች በመውሰድ በክልሉ በ 39 ወረዳዎች ደን የመከለል አፈጻጸማቸውን መሠረት በማድረግ የበጀት ድጋፍ በማድረግ አሳታፉፊ የደን አስተዳደር ማህበራትን የማደራጀትና የመደገፍ ልዩ አቅጣጫ እንደተያዘም ተገልፀዋል።
29 የችግኝ ጣቢያ ማዕከላትን የማጠናከር ሥራ እንዲሁም በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ክቡር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አቅጣጫ መሠረት በሀገር ደረጃ አስተዋፅኦ ማበርከት የሚችል ሞዴል ችግኝ ጣቢያ ለማደራጀት እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል።
ከፕሮጀክቱ ትልቁ ተግባራት መካከል የኑሮ ማሻሻያ አካል የሆነው ከቡና ገለባ ከሰል ማምረት የሚያስችል 3 ማሽኖች ወደ ስራ እንዲገቡና ህብረተሰቡ ከደን ጥገኝነት በማላቀቅ ኑሯቸውን ለማሻሻል እንደሚሰራም ተገልፀዋል ።
የኮሚቴ አባላት ባነሱት አስተያየት እስከ አሁን የተከናውኑ ተግባራት አበረታች መሆኑን ጠቅሰው በያዝነው የበጀት ዓመት በክልላችን ማህበረሰብ ዘንድ የቆየውን የደን አጠባበቅ ባህል ለማስቀጠል በየዘርፋችን ለፕሮጀክቱ መሳለጥ ተግተን እንሰራለን ብለዋል።
በመጨረሻም ለኑሮ ማሻሻያ ስራ ማስከጃ የሚሆን ተዘዋዋሪ ፈንድ ማንዋል ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን ወደ ትግበራ በሚያስገቡ ነጥቦች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተቋጭቷል።
በአሻግሬ ገ/ወልድ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
