ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በቦንጋ ከተማ እየተገነባ ያለውን የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤትና የተቋማት ቢሮዎች ህንጻ ግንባታ ሂደት ያለበትን ደረጃ ተመለከቱ




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በቦንጋ ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤትና የተቋማት ቢሮዎች ህንጻ ግንባታ ሂደት ያለበትን ደረጃ ምልከታ አድርገዋል።
የክልሉ መንግስት በ5.763 ቢሊዮን ብር ወጪ በክልሉ ብዝሃ ዋና ከተሞች የቢሮዎች ህንጻ ለመገንባት መሠረተ ድንጋይ በማስቀመጥ በይፋ ሥራ ማስጀመሩ የሚታወስ ነዉ።
ከእነዚህም መካከል በቦንጋ ብዝሃ ዋና ከተማ በ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚገነባዉ የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና የክልል ተቋማት ቢሮ ህንጻ ግንባታ ሂደት ያለበትን ደረጃ ርዕሰ መስተዳድሩ ተዘዋውረው ተመልክቷል።
በክልሉ ብዝሃ ማዕከላት እየተገነቡ የሚገኙ የተቋማት ቢሮ ህንጻዎች ሥራ ሲጠናቀቅ የመንግሥትና የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥን የሚያሳልጡ ናቸዉ።
በምልከታዉ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በፍቅር ከበደ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
