የብልፅግና ፓርቲ ያለፉት ዓመታት ጉዞዎችና የቀጣይ ዓመታት የትኩረት መስኮች ላይ ያተኮረ የዉይይት መድረክ እየተካሄደ ነዉ።

Spread the love

የብልፅግና ፓርቲ ያለፉት ዓመታት ጉዞዎችና የቀጣይ ዓመታት የትኩረት መስኮች ላይ ያተኮረ የዉይይት መድረክ እየተካሄደ ነዉ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ ክልል አቀፍ የከፍተኛ አመራር ውይይት በቦንጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥ብልጽግና ፓርቲና የሚመራዉ መንግስት ባለፉት ዓመታት በልማት፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ ፣ በዲፕሎማሲና በዴምክራሲ ግንባታ ተጨባጭ ዉጤቶችን ማስመዝገቡን ገልጸዋል።

በየደረጃው ያለው አመራር በለውጡ መንግሥት የተመዘገቡ ለውጦችን በማስቀጠል የህዝብ ተጠቃሚነት ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

በፓርቲዉ በተለዩ የርብርብ ማዕከላት ላይ በየደረጃው ያለው አመራር ወጥ አረዳድ በመያዝ በላቀ ተነሳሽነት መፈጸም እንደሚጠበቅበትም እንዲሁ።

በየደረጃው በተለዩ የመንግሥት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እንዲሁም በአንዳንድ ተቋማት የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዝርዝር በመገምገም ብልሽቶችን የማረም ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል።

በየደረጃው ያለው አመራር ፓርቲው ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ተምሳሌታዊ ሀገርነት ለማሻገር በሁሉም መስክ የጀመራቸውን ተግባራት በማስቀጠል ብሄራዊ ጥቅም ማስከበር እንደሚጠበቅበትም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት።

በመድረኩ ለዉይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ እየቀረበ ይገኛል።

በዕድገቱ በዛብህ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *