
በክልላችን የቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ በዞኑ ለጋቸብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደረጃውን የጠበቅ 4 የመማሪያ ብሎክ ልገነባ ነው።
ግንባታው ከ5.5 ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ወጪ ይገነባል።
በዞኑ “በትምህርት ለትውልድ” የትምህርት ቤት ማሻሻያ መርሀግብር ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቦ የመማሪያ ክፍሎች እየተገነቡ እንደሚገኝ ከዞኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
