ፓርቲዉ በወሰደው ቁርጠኝነት ክልሉ በአጭር ጊዜ የብልፅግና ተምሳሌት መሆን ችሏል – አቶ አደም ፋራህ



በብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የፓርቲ ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እንደገለጹት፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሁለት ዓመት ከአምስት ወራት ተምሳሌት የሆነ ውጤት ማስመዝገብ የቻለዉ ፓርቲው በወሰደዉ ቁርጠኛ አቋም ነው፡፡
የተቋማትን ዝግጁነት በቅንጅት መምራት፣ ያለምንም የሰላምና የጸጥታ ችግር ወደ ሥራ መግባት፣ መደበኛ አገልግሎቶች ሳይቆራረጡ መቀጠላቸዉ፣ ክልሉ በፋይናንስ ራሱን መቻሉ፣ ፈጥኖ ወደ ሥራ መግባትና የማስፈጸም አቅም መገንባት መቻሉ አሁን ለተመዘገቡ ስኬቶች መሰረት መሆናቸዉን አብራርተዋል፡፡
ብልፅግና ፓርቲ ሁሉን አቃፊና ሁሉን አሳታፊ ኅብረ ብሄራዊ ፓርቲ መሆኑን የተናገሩት አቶ አደም ፋራህ፣ በሙሉ እይታና በጥራት የመደመር ዕሳቤን መሰረት በማድረግ አሰባሳቢ ትርክት መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ሁሉን አባላት ማብቃትና ብቁ አደረጃጀት መፍጠር ያለውን ፋይዳ በመረዳት ለዚህ ስኬት በትኩረት ተሰርቷል ውጤትም ተገኝቶበታል ብለዋል፡፡
በየደረጃዉ ብቁ የሆኑ ስትራቴጂያዊ አመራሮችን ለማፍራት በርካታ ስልጠናዎችን በመስጠት ሀገራዊ ለውጡን መሸከምና ማስቀጠል የቻለ አመራር መፍጠር እንደተቻለም አንስተዋል፡፡
እንደ ፓርቲ በሁሉም መስኮች በተመዘገቡ ስኬቶችና ድሎች የሕዝብ ቅቡልነት ማረጋገጥ እንደተቻለ ያብራሩት አቶ አደም ወጥነት ያለው ተቋማዊ ስርዓት መዘርጋት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡
የአመራሩንና የአባሉን አቅም በስልጠና በመገንባት ወጥነት ያለውን ተቋማዊ አሰራር መዘርጋት እንደተቻለም ፓርቲው አስታውቋል፡፡
በግምገማ መድረኩ በፓርቲ ሥራዎች ባለፉት ስድስት ወራት በተመዘገቡ ስኬቶችና ውስንነቶች እንዲሁም በቀጣይነት ትኩረት በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ በስፋት ውይይት እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
https://www.linkedin.com/company/southwest-communications
በትሬድስ
https://www.threads.com/@southwest_communications
በብሉ ስካይ
