የአየር ኃይል ምስረታ በዓል የኢትዮጵያን ገፅታ በሚያጎላ መልኩ ይከበራል – ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ



የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የአየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የኢትዮጵያን ገፅታ በሚያጎላ መልኩ ይከበራል አሉ።
ዋና አዛዡ ከተቋሙ ከፍተኛ መኮንኖች ጋር ባደረጉት ውይይት እንዳሉት÷ በዓሉ ከመጪው ጥር 15 እስከ 19 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል የዘመናዊነትና የሉዓላዊነት አርማ ሆኖ የዘለቀበትን 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የሀገሪቱን ክብርና የተቋሙን ግዙፍ አቅም በሚመጥን መልኩ ለማክበር ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዓሉ አየር ኃይላችን የቴክኖሎጂ ቁንጮና የጥንካሬያችን መገለጫ መሆኑን በተግባር የምናሳይበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ብለዋል።
አከባበሩ ዝም ብሎ መታሰቢያ ብቻ ሳይሆን የተቋሙን የላቀ ቁመና ለዓለም የሚያሳይ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚፈጥር እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕዝብ በአየር ኃይል ላይ ያለው መተማመን እንዲጎለብት የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመንካት ለሚያስቡ ኃይሎች የተቋሙን ዝግጁነትና ቁመና ለማሳየት ያለመ እንደሆነም አመላክተዋል።
የአየር ኃይሉ ከፍተኛ አመራሮች በበኩላቸው÷ ተቋሙ በሪፎርም ታድሶና በዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች ተገንብቶ በሚገኝበት ወቅት 90ኛ ዓመቱን ማክበሩ ልዩ ትርጉም እንዳለው መናገራቸውን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
በዓሉን በላቀ የዲሲፕሊንና የዝግጁነት ደረጃ ለማክበር ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
https://www.linkedin.com/company/southwest-communications
በትሬድስ
https://www.threads.com/@southwest_communications
በብሉ ስካይ
