ፌስቡክ በመጠቀም የጥላቻና ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ የእስራት እና የገንዘብ ውሳኔ መቀጣቱን በዳውሮ ዞን የታርጫ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

Spread the love

ፌስቡክ በመጠቀም የጥላቻና ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ የእስራት እና የገንዘብ ውሳኔ መቀጣቱን በዳውሮ ዞን የታርጫ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

ተከሳሽ አስራት ወልዴ (ዶ/ር) የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንበት የቻለው ማኪራ ኮፊ፤ካፋ ቲየብ(kafa Tube እና Asrat Wolde በሚሉ ፌስቡክ አካውንት በመጠቀም የጥላቻ እና ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ጥፋተኝነቱ በማስረጃ በመረጋገጡ ነው፡፡

ተከሳሽ አስራት ወልዴ (ዶ/ር) ሀሰተኛ ማኪራ ኮፊ፤ካፋ ቲየብ(kafa Tube እና Asrat Wolde በሚሉ የፌስቡክ አካውንት በመክፈት ተከሳሹ ከነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮችን፤የተለያዩ የመንግስት ተቋማትን ፤የተቋሙን ባለሙያዎችን፤የብሔር ስም በመጥቀስ ግጭት ቀስቃሽ ጽሁፎችን በማሰራጨት ወንጀል ክስ ቀርቦበታል፡፡

የታርጫ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ህግ ግለሰቡን የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1185/2012 ዓ.ም በአንቀፅ 7 ንዑስ አንቀፅ ከ1 እስከ 5 ስር ያለውን ድንጋጌ በመተላለፍ ወንጀል ክስ መስርቶበታል፡፡

የታርጫ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ህግ በግለሰቡ ላይ የመሰረተውን ሀሰተኛ እና የጥላቻ ንግግር ክስን ግራ ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች ተከሳሹን ጥፋተኛ ነው ሲል የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል፡፡

ዐቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው የቅጣት ማክበጃ ግለሰቡ በፈፀመው በጥላቻ ንግግሩ ምክንያት በግለሰቦች እና በተቋማት ላይ ጥቃት በመፈፀሙ የመንግስትን የስራ ኃላፊዎችን በመጥቀስ እና ብሔርን ከብሔር ግጭት ቀስቃሽ ጽሁፎችን በማስራጨት ቅጣቱ ከብዶ እንዲወሰንበት ፍርድ ቤቱን ሲጠይቅ ተከሳሹ በበኩሉ የቤተሰብ አስተዳደሪ እና አቅመ ደካማ ሰዎችን የሚረዳ ነኝ ስለዚህ ቅጣቱ ቀሎ እንዲወሰንበት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

የታርጫ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዐቃቤ ህግን የቅጣት ማክበጃ አንዱን ተቀብሉ የተከሳሹን የቅጣት ማቅለያ ሁለቱን በመቀበል እና በቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት እና በወጣውን አዋጅ ቁጥር 1185/2012 ዓ.ም በአንቀፅ 7 ንዑስ አንቀፅ 4ን መሰረት በማድረግ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

በዚሁ መሰረት የታርጫ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ባስቻለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹን እና ሌሎችን ያስተምራል ተከሳሽ አስራት ወልዴ (ዶ/ር) በሁለት አመት ፅኑ እስራትና በአምስት ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡

በሀሰተኛ ስም በመጠቀም አይደረስብኝም ብሎ የነበረው ግለሰብ በህግ ውሳኔ መሰጠቱ ማንም ቢሆን ራሱን የደበቀ ቢመስለውም ከህግ ማምለጥ እንደማይቻል ማሳያ ነው

በመሆኑም በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች ሀሰተኛ ስም በመጠቀም የመንግስት ኃላፊዎችን እና ተቋማት ስም በማጠልሸት ተግባር ተሰማርተው ያሉ ጥቂት ግለሰቦች ላይ የተጀመረው ክትትል ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አውቀው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል፡ ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ዘግቧል፡፡

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

📌በትሬድስ

https://www.threads.com/@southwest_communications

📌በብሉ ስካይ

https://bsky.app/profile/swc79.bsky.social

በደብልው ኤን ሶሻል

https://wnsocial.com/page/16775

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *