የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የዘመን መለወጫን በማስመልከት ለ745 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የዘመን መለወጫን በማስመልከት ለ745 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት፣ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በክልሉ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሕግ ፍርዳቸውን ሲፈጽሙ የቆዩ 745 ታራሚዎችን በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን አስታወቀ።

ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል 720ዎቹ ወንዶች ሲሆኑ 25ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው። ውሳኔው የክልሉ የይቅርታ ቦርድ፣ ታራሚዎቹ ካቀረቡት የይቅርታ ጥያቄ በመነሳት፤ በይቅርታ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያዎች መሰረት መስፈርቱን የሚያሟሉትን በጥልቀት መርምሮ ለክልሉ መንግስት ካቀረበ በኋላ የተላለፈ መሆኑ ተገልጿል።

የይቅርታ ቦርዱ በምርመራው ወቅት የመንግሥትን፣ የህዝብንና የታራሚዎችን ጥቅም ባገናዘበ መልኩ ግምገማ ማድረጉ ተጠቁሟል።

የይቅርታ ተጠቃሚ የሆኑት ግለሰቦች በማረሚያ ተቋም በነበራቸው ቆይታ በመልካም ሥነ ምግባራቸው መታረማቸውንና መታነፃቸውን የሚያረጋግጥ በቂ መረጃ ከየደረጃው ከሚገኙ የጸጥታ ተቋማት የቀረበላቸው መሆኑም ተረጋግጧል።

በዚህም መሰረት የክልሉ መንግስት፣ ከእስር የሚለቀቁት ታራሚዎች ከዚህ በኋላ ለህብረተሰቡ የስጋት ምንጭ ሳይሆኑ ሰላምን የሚሰብኩ፣ አምራችና ህግ አክባሪ ዜጎች በመሆን ማህበረሰቡን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።

ህብረተሰቡም የእነዚህን ዜጎች መታረምና መታነጽ ተገንዝቦ እንዲቀበላቸውና እንዲያግዛቸው ያሳሰበው መንግስት፣ ከእስር ከወጡ በኋላ የይቅርታውን ዓላማ የሚስቱና በድጋሚ ህግን የሚጥሱ ካጋጠሙም፣ ህብረተሰቡ በተለመደው መልኩ ለፍትህ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ መልዕክቱን አስተላልፏል።

በመጨረሻም፣ የክልሉ መንግስት ለመላው የክልሉ ህዝቦችና ለይቅርታ ተጠቃሚዎቹ መልካም አዲስ ዓመት ተመኝቷል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *