




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የክልልና የዞን ምክር ቤቶች 5ተኛ ዙር የጋራ ምክክር ፎረም በታርጫ ከተማ አካሂደዋል።
ፎረሙን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፌ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ የምክክር ፎረሙ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን የሚያጠናክር እና የሚያፀና ነው ብለዋል።
ዋና አፈ ጉባዔው በክልሉ የሚገኙ ምክር ቤቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በአሠራር መሻሻል እንደመጣ በመጠቆም ለቀጣይም ምክር ቤቶች ተጠናክሮ አንደምቀጥሉም ገለፁት።
የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በፎረሙ ተገኙተው ምክር ቤቶች ህግ አውጪ ህግ ተርጓሚ ህግ አስፈፃሚ አንድ ላይ ሆነው በጋራ መሥራ መወያየት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋወሳኝ ተግባር ነው በማለት መንግሰታችን የነደፈውን የተለያዩ ተልዕኮ ከማሰፈፀም አንፃር የጎላ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።
የዳውሮ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዳዊት ሚኖታ ለ5ተኛ ዙር የምክክር ፎረምን ለመታደም ለመጡ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት በማስተላለፍ ምክር ቤቶች የህዝብ ውክልና ተቀብሎ ከሚያሰፈጽሙበት መንገድ አንዱ ከባለድረሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የህዝብን አንድነት የሚያጠናክሩ ተግባራት በሰፍው ይሰራልም ብለዋል።
የምክክር ፎረሙ እሰከ ቀበሌ ማዕከል ድረሰ በምክርቤት ተሳትፎ የተሰሩ የልማት ተግባራትን በዳውሮ ዞን ማርማንሳ ማሪ ጉታ ቀበሌ ጉብኝት እንደሚደረግ ገልፀዋል።
በፎረሙ የምክር ቤቱ የ4ተኛ ዙር ምክክር መድረክ ቃል ጉባኤ ቀርቦ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።
