




የኮሚሽኑ ዋና ጽ/ቤት ከክልሎችና ከተማ አስተዳደር የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊዎች ጋር በመሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ስራዎችን መገምገም ጀምሯል።
በፓርቲው ዋና ፅ/ቤት እየተካሄደ በሚገኘው የአፈጻጸም ግምገማ መርሐ ግብር ላይ የኮሚሽኑ ጸሐፊና የጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሀብታሙ ሲሳይን ጨምሮ ሌሎች የኮሚሽኑ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።
የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረኩን የመሩት የኮሚሽኑ ጸሐፊና የጽ/ቤት ሃላፊ ክቡር አቶ ሀብታሙ ሲሳይ ሲሆኑ የክልልና የከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊዎች የዘጠኝ ወር አፈጻጸም ሪፓርት አቅርበው ውይይት እየተደረገባቸው ነው።
በውይይቱ ላይ እንደተመለከተው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ኮሚሽኑ በትኩረት ባከናወናቸው ስራዎች በአባላቱ ዘንድ የፓርቲውን አመኔታ አድጓል፣ በፓርቲ ስነ ምግባር የታነፁ አመራሮች እና አባላት ማፍራት ተችሏል፣ ፀረ ሙስና ትግል በተቀናጀ መንገድ በማከናወን ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መታየት ጀምረዋል።
የግምገማ መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚከናወን ሲሆን በቀጣይ መርሐ ግብር የበጀት አመቱ ቀሪ ወራት እቅዶችና በአዲስ መልክ በተዘጋጀው የኮሚሽኑ ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ጠንካራ ኢንስፔክሽን፤ ለጠንካራ ፓርቲ!
