የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

Spread the love

የመንግስት ተቋማትን የመጀመሪያ ሩብ አመት የ100 ቀናት የሪፎርምና ዋና ዋና የኢኮኖሚ ዕቅድ አፈጻጸም ዛሬ መገምገም ጀምረናል፡፡

በቆይታችንም በ100 ቀናት የትኩረት ማዕከል የሆኑ አበይት ተግባራት ላይ የተገኙ ዉጤቶችን እና የታዩ ክፍተቶችን ከተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ እናያለን፡፡

የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበት አይዘነጋም፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የሪፎርሙን ውጤት ለማስቀጠልና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በቀጣይ ትኩረት በሚደረግባቸው ጉዳይ ላይ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል፡፡

በዚህ ሩብ አመት ሀገራችን ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም የገባችበት በመሆኑ በዚሁ መድረክ ለየት ባለመልኩ የታዩ ለውጦችን እንዲሁም ፈተናዎችን በተሟላ ሁኔታ ማሳየት የሚያስችል ግምገማ እናካሂዳለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *