19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች ህዝቦች በዓል ቀን በድምቀት ማክበር እንዲቻል ባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል፦ አፈጉባኤ ወንድሙ ኩርታ

Spread the love

“ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት ” በሚል መሪ ቃል 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ቀን ባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸው አፈ ጉባኤ ወንድሙ ኩርታ አሳስበዋል ።

“ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት ” በሚል መሪ ቃል 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ቀንን ምክንያት በማድረግ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሁለቱም ምክርቤቶች በተዘጋጀ መሪ ዕቅድ ላይ አብይ ኮሚቴ ተወያይተዋል።

ዘንድሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት ” በሚል መሪ ቃል 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ቀን በአርባምንጭ ከተማ ህዳር 29/2017 ዓ/ም ይከበራል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልም በዓሉን በደመቀ ባህላዊ ኹነቶች እንዲከበር የሚያስችል የመነሻ ዕቅድ በብሔረሰቦች ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ አቅርበዋል።

ዋና አፈጉባኤው ባቀረቡት መነሻ የውይይት ዕቅድ የበዓሉ መከበር ብዝሃነትን በማስተናገድ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህገ መንግስታዊ ዋስትና የተረጋገጠበት ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

በዓሉ መከበሩ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ባህላቸውን እንዲያስተዋውቁ ዕድል የሰጠ መሆኑንም አቶ መቱ አኩ አብራርተዋል ።

በክልሉ የሚከበረው ይኸው በዓል ከባለፈው ዓመት ተሞክሮ በመውሰድና ጉድለቶችን በማረም በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ትኩረት በመስጠት ማክበር እንደሚገባ አቶ መቱ አሳስበዋል ።

የክልሉ ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ በበኩላቸው በ18ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች ህዝቦች በዓል አከባበር ወቅት የነበሩ ጠንካራና ጉድለት የታየባቸውን አፈጻጸም ለዘንድሮው መነሻ እንዲሆን በማስታወስ ለተሳታፊዎች የነበረውን አፈጻጸሙን አቅርበዋል ።

የዘንድሮው 19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች ህዝቦች በዓል ቀን ባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት በመስጠት ከወዲሁ ለተፈጻሚነቱ በኃላፊነት ሊመሩት እንደሚገባ አፈ ጉባኤ ወንድሙ ኩርታ አሳስበዋል ።

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ይበልጥ ለማዳበር በክልሉ የሚገኙ ብሔሮች ብሔረሰቦች ተቀራራቢነት ያላቸው አካባቢዎች ጋር በቅንጅት የሚያከብሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባልም ብለዋል።

በ19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች ህዝቦች ቀን አከባበር ብሔረሰቡን የመሰለ ባህላዊ ክዋኔዎችን በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባም አፈጉባኤ ወንድሙ ኩርታ ተናግረዋል ።

በክልሉ ያሉ ሚዲያዎች የበዓሉን አከባበር በተመለከተም ያልተቆራረጠ መረጃ ለህዝቡ ተደራሽ ከማድረግ አንጻር በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም አጽንኦት በመስጠት አሳስበዋል ።

በዕለቱም የሁለቱም የክልሉ ምክርቤቶች አፈጉባኤዎች፣ የበዓሉ አዘጋጅ አብይ ኮሚቴ አባላት፣ የሚዲያ ተቋማትና የዞን አፈጉባኤዎች በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል።

በነበረው የውይይት መድረግ በዓሉን በላቀ ድምቀት ለማክበር እንዲያስችል የተለያዩ መሠረታዊ ጥያቄዎችን በማንሳትና በመመካከር ለተግባራዊነቱ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት በመግባባት ውይይቱ ተቋጭቷል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *