“የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት በሚል መሪ ሀሳብ መነሻ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በየደረጃው ለሚገኙ ለክልላችን ብልጽግና ፓርቲ አመራር አካላት ሲሰጥ የነበረው የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

Spread the love

የዚህ ስልጠና ዋናው አላማ አርቆ በማሰብና አልቆ በመስራት በሁሉም መስክ እመርታን ማስመዝገብ እንዲቻል አመራሩን በፓርቲያችን ህልምና ትልም ዙሪያ መግባባትን መፍጠር፤ የመፈፀም ብቃቱ የጎለበተ አመራር ለመፍጠር አቅም መገንባትና የአስተሳሰብና ተግባር አንድነትን ለማምጣት ታስቦ የተሰጠው ስልጠና በጥሩ መንፈስ ተጠናቋል።

ከዚህ ስልጠና በኋላ አመራሩ ቁጭትና መነሳሳትን በመፍጠር አቅሞችን ወደ ውጤት ለመቀየር፣ በየደረጃው ለሚነሱ ጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠትና ማህበረሰባዊ ለውጥ ለማምጣት ከትናንት ይልቅ ለነገ ተግቶ መስራትን ቁልፍ አጀንዳ እንደሚያደርገው ይታመናል፤ ይሳካልም።

ለዚህ ደግሞ የአመራሩ ከፍ ያለ ሚና እንደነበረ ሆኖ ማህበረሰባችንም የሚጠበቅበትን በሙሉ አቅሙ በመወጣት የተገኙ ውጤቶችን በማስፋት ችግሮችን መሻገርና ሁለንተናዊ እድገትን በግለሰብና በማህበረሰብ ደረጃ ለማስመዝገብ ጥረት ሊያደርግ ይገባል።

ስልጠናው ቀጣይ ከጥቅምት 12/2017 ዓ/ም ጀምሮ በዞን ማዕከል ደረጃ ለወረዳና ከተማ አስተዳደር አመራሮች የሚሰጥ ሲሆን ለአባሎቻችንም በተልእኳቸው መሠረት የሚቀጥል ይሆናል ።”

አቶ ነጋ አበራ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *