



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የሚደገፍ የጎጀብ እና ታርጫ ምርምር ንዑስ ጣቢያዎች የመስኖ ጥናትና ዲዛይን ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ በኃላ በኢንስቲትዩቱ ግቢ እየታሰሩ ያሉ ተግባራትን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የኢንስቲትዩቱን ግቢ የተሰሩ ለምርምር የሚያግዙ ስራዎችን የተመለከቱት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አስተያየታቸውን ስጥተዋል ።
በምርምር ኢንስቲትዩት ግቢ እየተሰሩ ያሉ የቨርሚ ኮምፖስት አዘገጃጀት፣ የተለያዩ የእርሻ የምርምር ስራዎችንና የማሳ አያያዝ እንደተሞክሮ በመውሰድ በራሳቸው ማሳ ለማዘጋጀት እንዳነሳሳቸው በአስተያየታቸው ገልጸዋል።
የተመረጡ ግደሮችን ለማባዛት በማሰብ በምግብ ማጠናከሪያ ፕሮግራም የተገነባው ግንባታ ወደ ስራ ሲገባ በአካባቢው ብሎም በክልሉ ውስጥ የእንስሳት ዝሪያን በማሻሻል የወተት ምርትን ለማሳደግ አይነተኛ ሚና መኖሩን ተናግሯል።
በኢንስቲትዩቱ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አርሶ አደሩንና አልሚዎችን ቴክኖሎጂን ለመቀመርና ወስዶ በመተግበር ገቢያቸውን ለማሳደግ ሚናው ከፍ ያለ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል ።
የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል አለሙ የክልሉ አቅም መነሻ በማድረግ በግብርናውን ዘርፍ የሚታዩ ማነቆዎችን በምርምር ለመፍታት ተቋሙ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል ።
ከቴክኖሎጂዎቹ አንዱ የቨርሚንግ ኮምፖስት አዘገጃጀት መሆኑን በማንሳት ይህም የአፈር አሲዳማነትን ለመቀነስ እንደሚያግዝ፤
የኦርጋንክ ማዳበሪያ አጠቃቀምን እንደሚበረታታ፣ ወጪንም በመቀነስ የኢኮኖሚ አዋጭነት መኖሩን አንስተዋል ።
የጉብኝቱ ዓላማ የተፈጥሮ ማዳበሪያ አዘገጃጀት ለመጡ አመራር ፣ አርሶ አደርና አልሚ ባለሀብቶች በማሳየት በራሳቸው ማሳ እንዲተገብሩ ለማበረታታት ጉብኝቱ መሆኑን ገልጸዋል።
በርካታ መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጎበኘት ሀሳብና ልምድ እንዲቀስሙና ከተቋሙ ምክረ ሀሳብ በመውሰድ እንዲያሰፉ ለማድረግ እንደሚያግዝ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል ።
በመጨረሻም የግብርናው ባለድርሻ አካላት ያለ ምርምር ምርታማነትን ማሳደግ እንደማይቻል በመገንዘብ ተቋሙ በመነሻነት የሚያወጣውን ተክኖሎጂን ተቀብሎ በክልሉ በማስፋት አንጻር ድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል ።
የክልሉን ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የምግብ ስርዓት ማጠናከራሪያ ማኔጀር የሆኑት ዶ/ር አብይ ገ/ሚካኤል በፕሮግራሙ የተለያዩ እየተሰሩ ያሉ መሠረተ ልማቶችን መኖሩን በማንሳት ከነዚህም አንዱ የሆነውን በ27 ሚሊየን ብር ግንባታው የተጠናቀቀውን የ100 ጊደር ማባዣ በረትን ማሳየት እንደሆነ በማንሳት በበጀት የደገፉ አካላትን አመስግነዋል ።
የግንባታው ዓላማ የተሻሻሉ የእንስሳት ዝሪያዎችን ከውጭ በማምጣት በማባዛት ጊደሮችን ለአርሶ አደሩ ማሰራጨት እንደሆነ በማንሳት ጤናቸውን ለመጠበቅም በቀጣይ የእንስሳት ክሊንክ ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀምር ዶ/ር አብይ ጠቁመዋል ።
የቦንጋ ግብርና ምርምር ዳይክተር የሆኑት አቶ ዘላለም አባቴ በተቋሙ የተለያዩ የምርም ተግባራት በአራቱ ዞኖች በሰብል ልማት፣ በተፈጥሮና እንስሳት እርባታ እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል ።
ቴክኖሎጂ ማፍለቅ፣ ማላመድና ለአርሶ አደሩ የማስተዋወቅ ከተዋወቁ በኃላ ዘርን ለአባዢ ድርጅቶች የማሰራጨት ስራ ይሰራል ነው ያሉት።
በዚህም በጎጀብ ምርምር ጣቢያ ለዘር ብዜት የሚሆን ሩዝ 375 ኩንታል ማምረት መቻሉን፣20ሺ በላይ የቡና ችግኝ፣7ሺ የሚሆኑ የተሻሻሉ አቮካዶ ዝሪያ ያላቸውን ችግኞችን በማፍላት ለአርሶ አደሮች ማሰራጨት መቻሉን ለአብነት አንስተዋል።
በጌታሁን ግርማ
