እንደ ሰንደቅ ዓላማ ያሉ የጋራ እሳቤ የሚያሰርጹ፣አንድነታችን እና አብሮነታችን የሚያስተሳስሩ የጋራ ጉዳዮችን በየጊዜው መዘከር እና ከፍ ማድረግ ይገባናል -ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ( ዶ/ር)

Spread the love

‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔራዊ ሰንደቅዓላማ ቀን በተለያዩ ስነ-ሥርዓቶች በቦንጋ ከተማ ተከብሯል።

በክልሉ የዘንድሮ 18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ”ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ህዳሴ!” በሚል መሪ ሀሳብ ተከብሮ ውሏል።

በአከባበር ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እንደገለፁት፤ ኢትዮጵያ ብዙ ብሔር ብሔርሰቦችና ህዝቦች የሚገኙባት ምንም እንኳን በብሔር፣ በጎሳና በቋንቋ ቢለያዩም የጋራ የሚያደርጋቸው በርካታ እሴቶች ያላት ታላቅ ሀገር ናት።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ አንድነታችን እና ሉዓላዊነታችን የሚናስታውስ የድሮ አባቶች ታግለው የሀገራችን ክብር አስጠብቆ ያቆዩ ትልቁ የአብሮነታችን አርማ ነው ሲሉም ተናግረዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።

ኢትዮጵያዊያን በጋራ ተባብረው እና ተረዳድተው በድል ያስመረቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችንን እንደ ስንደቅ ዓላማችን የጋራ ገዥ ትርክት የሚገነባ የወል ሀብት እንደሆነም በወቅቱ ጠቅሰዋል።

እንደ ሰንደቅ ዓላማ ያሉ የጋራ እሳቤ የሚያሰርጹ፣አንድነታችን እና አብሮነታችን የሚያስተሳስሩ የጋራ ጉዳዮችን በየጊዜው መዘከር እና ከፍ ማድረግ እንደሚገባም ዶክተር ነጋሽ ዋጌሾ አስገንዝበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማከልም የአሁኑ ትውልድ የሀገራችን የነጻነት ምልክትና የሉዓላዊነታችን መለያ የሆነውን ሰንደቅዓለማ ክብር እና ልዩ ቦታ በመስጠት በየጊዜው መዘከር እና ከፍ ከፍ ማድረግ ይገባቸዋል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

በክብረበዓሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ስነስርዓትም

አከናውነዋል።

በወቅቱ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣የካፋ ዞን ከፍተኛ አመራሮች የመንግስት ሠራተኞች፣የፀጥታ አካላትና ሌሎች አካላት ተገኝተዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *