የድሮ አባቶቻችን ደምና የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ጠብቆ ያቆዩልንን ሰንደቅ አላማ የአሁኑ ትውልድ ጠብቆ የማስቀጠል አደራ እንዳለበት ተገለጸ

Spread the love

ዘንድሮ ለ18ኛው ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ በፓናል ውይይት እና በተለያዩ ስነስርአቶች እየተከበረ ነው

ቀኑ”ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!”በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረ የሚገኘው።

በስንደቅ ዓላማ ቀኑ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የካፋ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ግርማ ደፋር አንድ ሀገር እንደሀገር ሲመሰረት የዛ ሀገር ትልቁ ምልክት ሰንደቅ ዓላማ ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደሀገር ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ የሀገራችን ስንደቅ ዓላማ የሀገራችን የነጻነት ምልክት፣ የሉዓላዊነት መገለጫ፣መከበሪያ፣ ለሀገር ክብር ብዙዎች የተዋደቁበትና መስዋዕትነት የከፈሉበት ትልቁ መገለጫችን በመሆን ቆይቷል።

የድሮ አባቶቻችን የደምና የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ጠብቆ ያቆዩልንን ሰንደቅ አላማ የአሁኑ ትውልድ ጠብቆ የማስቀጠል አደራ እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተውበታል።

በቦንጋ ከተማ የዘንድሮ ሰንደቅ ዓለማ ቀኑን በማስመልከት የተዘጋጀ ሰነድ በክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ቢሮ ኃላፊ በአቶ ንጉሴ ወ/ ጊዮርጊስ እየቀረበ ይገኛል።

ከሚቀርበው ሰነድ መነሻ ከሚደረገው ውይይት ባሻገርም የሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ሰነ-ሥርዓትም ይከናወናል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *