




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከስር መዋቅሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በአስር ዓመት መሪ ዕቅድ ክለሳ፣ በ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ ማካሄድ ጀምረዋል።
ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት እንደሚደረግ የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል ።
በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አባላት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ የከፍተኛ፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ፕሬዝዳንቶችና ምክትል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ለሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
በጌታሁን ግርማ
