የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

Spread the love

መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ምክር ቤቱ የክልሉን አስፈፃሚ አካላት ተግባር በየደረጃው በመገምገም የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል።

አክለውም የመድረኩን አላማ በማስረዳት፣ የአፈፃፀም ሪፖርቱ የምክር ቤቱን ደንብ በጠበቀ መልኩ እንዲቀርብ አሳስበው መድረኩን በይፋ አስጀምረዋል።

በዚህም መሰረት ህግ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር፣ ግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች፣ በጀትና ፋይናንስ፣ ከተማና መሠረተ ልማት እንዲሁም ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች በየዘርፉ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

መድረኩ ለተከታታይ 2 ቀናት እንደሚካሄድ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በመድረኩ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ፣ ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፀሀይ ደርጫን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ አመራሮችና የየዘርፉ ባለሙያዎች እየተሳተፉ እንደሚገኙ የደቡብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *