ክልላዊ የሻይ ተክል ኢኒሼቲቭ ጅማሮው ያለበት ደረጃ የተሻለ መሆኑን ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ገለጹ

Spread the love

ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በሀገራችን ሶስት ሰፋፊ የሻይ ልማት እርሻዎች አሉ፣ ሁለቱ በክልላችን ይገኛሉ፤ እነሱም ውሽ ውሽና ጨዋቃ ናቸው ብለዋል።

ይሁን እንጂ አርሶ አደሮቻችን በዚህ ተክል ልማት ዙሪያ በሰፊው የገቡበት ሁኔታ አልነበረም ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

አቶ ማስረሻ በላቸው ከዘንድሮ ክረምት ጀምሮ ችግኝ በማዘጋጀት ለተከታታይ አመታት እንደ ክልል ልዩ ትኩረት በመስጠት ለመስራት በዝግጅት ላይ እንገኛለን ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አጋርተዋል።

ከሰፋፊ የሻይ ችግኝ ጣቢያዎች መካከል ካፋ ዞን ፣ገዋታ ወረዳ ቦጊንዳ ችግኝ ጣቢያ የዝግጅት ምዕራፍ ያለበት ደረጃ የሚበረታታ መሆኑንም አቶ ማስረሻ በላቸው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ዘንድሮ በክልሉ ተግባራዊ ከሚደረጉ ክልል አቀፍ ኢኒሼቲቮች ውስጥ የሻይ ተክል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *