



የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዲዮን ሳር በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ጊዲዮን ሳር ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው የኢትዮጵያ እና እስራኤልን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ውይይቶችን ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
