የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ በ2ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላለፈ

Spread the love

የሥራ አመራር ቦርዱ በአንደኛ አጀንዳነት የተወያየዉ የሚዲያ ኔትወርኩ የ2017 በጀት ዓመት የአስካሁን አፈጻጸም በተመለከተም ተቋምና የሰው ኃይል አደረጃጀት እና ለሥራው አስፈላጊ ግብዓት ማሟላትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ገምግሟል።

ሚዲያ ኔትዎርኩ ተቋማዊ አደረጃጀት ማለትም ብቃት ያለው የሰው ሀይል ማሟላት፣ የፋይናንስ እና በጀት አጠቃቀም፣ ለሥራው አስፈላጊ ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ኔትወርኩ በሙሉ አቅም ሥራ እንዲጀምር እየተደረገ ያለዉ እንቅስቃሴ ውጤታማ በመሆኑ መጠናከር እንደሚገባም ገምግሟል።

በሁለተኛ አጀንዳነት የሚዲያ ኔትዎርክ ወደ ተሟላ ሥራ የሚገባበት እና አየር ላይ የሚወጣበት ሁኔታ ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን ኔትወርኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ የማህበራዊ ሚዲያ ሥራውን እንዲጀምር ዉሳኔ አስተላልፏል ። በአየር ላይ መዉጣት የሚችልበት መንገድ አስፈላጊ ብቁ ቅድመ ዝግጅቶች እንዲደረጉ እና ከተለያዩ ሚዲያዎች ጋር በቅንጅት እንዲሰራም ቦርዱ አቅጣጫ አስቀምጧል።

የቦርዱ አባላት በመጨረሻም የሚዲያ ኔትወርኩ መሪ ቃልና ሎጎ ላይ የተወያየ ሲሆን ሌሎች ቀጣይ መሰራት በሚገባቸዉ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ዉሳኔዎችን አስተላልፏል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *