የመደመር መንግሥት ጥበብ ለሀገር ብልጽግና እና እድገት የማይተካ ሚና እንዳለው በግልጽ አስቀምጧልSAXDS

Spread the love

የመደመር መንግሥት ጥበብ ለሀገር ብልጽግና እና እድገት የማይተካ ሚና እንዳለው በግልጽ ማስቀመጡን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ገለጹ።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በተዘጋጁ የጥበባት እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ረቂቅ ፖሊሲ፣ ሌሎች የህግ ማዕቀፎችና በጸደቁ የአሰራር መመሪያዎች ላይ ከሚመለከታቸው የዘርፉ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ሲያካሂድ የቆየው ውይይት ተጠናቋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካ በዚሁ ወቅት፤ ጥበብን ለአሰባሳቢ ትርክትና ብሔራዊ ጥቅም መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ቱባ ባህሎች ያላት ትልቅ ሀገር መሆኗን ገልጸው፤ ባህልን የሚበርዙ ነገሮችን በጋራ መከላከል ይገባል ነው ያሉት።

መንግስት ከየትኛውም ጊዜ በላይ ለባህላዊ እሴቶች እና ለጥበብ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገልጸዋል።

በዚህም ዘርፉን በመሰረተ ልማት፣ በአደረጃጀትና በስርዓተ ትምህርት በማካተት ውጤታማ ስራ መስራቱን ተናግረዋል።

የመደመር መንግሥት ኪነ-ጥበብ ለሀገር ብልጽግና እና እድገት የማይተካ ሚና እንዳለው በግልጽ ማስቀመጡንም ነው ጨምረው የገለጹት።

በዘርፉ እየተዘጋጁ ያሉ ማዕቀፎች የዘርፉን ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ መሆናቸውን አንስተው፤ በቀጣዮቹ ጊዜያትም ከዘርፉ ተዋንያን ጋር በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

በማጠቃለያ መድረኩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልመሀዲ፣ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻህፍት ዋና ዳይሬክተር ሰርጸ ፍሬስብሀት፣ አንጋፋ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የክልል የባህልና ስፖርት ቢሮ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *