



ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት በምክትል ርመስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ እንደተናገሩት ብልፅግና ፓርቲ ከተመሰረተበት ቀን ጀምሮ የአመራርና የአባላትን አቅም በመገንባት ለሁለንተናዊ ብልጽግና እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በየወቅቱ የአመራሩንና የአባላቱን አቅም በመገንባት ለተሻለ ተልዕኮና አመራር ሲያዘጋጅ መቆየቱን ገልጸው ስልጠናው የአባላቱን የአመለካከትና የተግባር አንድነት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።።
ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ተገልፃል።
