የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የቴፒ ብዝሀ ማዕከል የብልጽግና ፓርቲ ህብረት የመንግስት ሠራተኛ አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጀመረ

Spread the love

ስልጠናው “በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።

ስልጠናው በመደመር መንግስት እይታ በግብርና መዋቅራዊ ትራንስፎርሜሽን ፣የኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ፣የከተማ ልማት እንዲሁም የቱሪዝም ዘርፍ እመርታ በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ያተኩራል።

​የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፀጋዬ ኃይሌ፣ ስልጠናው በአመራሩና በአባላት መካከል የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን መፍጠርን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

​ስልጠናው የአባላትን እውቀት፣ ክህሎትና አቅም ከመገንባት ባለፈ፣ የፓርቲውን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

በስልጠና መርሃ ግብሩ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፀጋዬ ኃይሌ “የከተማ ልማት እመርታ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ እያቀረቡ ይገኛሉ።

የከተሜነት ስሜትን በመላበስ የከተማ ክትመትን በማረጋገጥ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማምጣት ላይና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር እንደሆነ እያብራሩ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *