



በ2017 ዓ/ም በወረዳዉ በ8 ቀበሌዎች፣በተቋማትና በአርሶ አደር ማሳ 151 ሄክታር የለማ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት የመሰብሰብ ስራ በይፋ ተጀመረ::
ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በወረዳው የበጋ መስኖ ስንዴ በተከታታይ ዓመት በማልማት ውጤታማ መሆን ተችሏል ሲሉ በእለቱ በሃማኒ ቀበሌ የተገኙት የጊምቦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ትብብሩ አሰፋ ገልጸዋል::
ምርትና ምርታማነት በመጨመር ሀገራችን ኢትዮጵያ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የምታደርገውን ጉዞ እውን ለማድረግ በወረዳው ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ያሉት አስተዳዳሪው በወረዳው የበጋ መስኖ ስንዴ የሚለማባቸው ቀበሌዎች ወቅቱን ጠብቆ ምርት በመሰብሰብ ተጠቃሚ መሆን አለባቸው ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል::
በአርሶ አደር ማሳ፣በተቋማት እና በተለያዩ አደረጃጀቶች በበጀት ዓመቱ 151 ሄክታር ማሳ 160 አርሶ አደሮችን እና አደረጃጀቶች በበጋ ስንዴ መሳተፍ የቻሉ ሲሆን የአፈር ለምነትን የማከም፣የተሻሻለ ዘር በመጠቀምና በአካባቢዉ የሚገኙ የዉሃ አማራጮችን በመጠቀም የማሳ ልየታ በማድረግ ማልማት መቻሉን የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መብራቱ ገ/መድህን ገልጸዋል።
በዘንድሮ የበጋ ስንዴ የተሻለ ምርት መታየቱን የገለጹት የሃማኒ ቀበሌ አርሶ አደር አቶ ካሳሁን ገ/የሱስ እርሻን በሜካናይዜሽን በማረስና አስፈላጊ ግብዓቶችን በመጠቀማቸዉ ምርቱ የተሻለ መሆኑን ነው የተናገሩት።
ምርትና ምርታማነት ለመከታተል እንዲያመች የደረሰዉን ምርት በአንድ ማዕከል በመዉቃትና የተገኘዉን ዉጤት የሚገመገምበት ሁኔታ ይኖራል ማለታቸዉን የጊምቦ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።
