




የማስጀመርያ ፕሮግራሙ የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አከባቢዎች ቢሮ ከግብርና ቢሮ እና LLRP ጋር በመቀናጀት በምዕራብ ኦሞ ዞን መዔኒት ሻሻ ወረዳ ውጅናለሙ ቀበሌ የተጀመረ ሲሆን በተመሳሳይ ሰዓት በ8 የአርብቶ አደር ወረዳዎች ላይ መጀመሩን ዘመቻውን በይፋ ያበሰሩት የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አከባቢ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምሩ ቦኒ ገልፀዋል ።
አቶ ታምሩ አክለው ይህ ዘመቻ ለአርብቶ አደሩ የመኖር ህልውና የሆነውን እንስሳት ከመታደጉም በላይ የሰዎችን ጤንነት የማስጠበቅ ዘመቻ በመሆኑ ማህበረሰቡ በየማዕከሉ ከብቶቻቸውን በመቅረብ እንድያስከትቡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አማካሪ እና ግብርና ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊና አቶ ዮሐንስ መላኩ በበኩለሰቸው ክትባቱ እጅግ ትኩረት የሚሻና በአንድ ሳምንት የሚጠናቀቅ ስለሆነ ባለሙያዎች እና ልዩ ስልጠና የወሰዱ ተሳታፊዎች በቁርጠኝነት እንዲሰሪ ስሉ አስገንዝበዋል።
ለዘመቻው ስኬት ርብርብ ያደረጉትን አካላት በአርብቶ አደሩ ስም ያመሰገኑት የምዕራብ ኦሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ኬኒ በበኩላቸው የአርብቶ አደራችን እንስሳት ከበሽታው ለማትረፍ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ አድንቀዋል።
የመኒት ሻሻ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ዳዊት በበኩላቸው በሽታው ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በእጃቸው ባለው መድኃኒት ርብርብ ስያደርጉ መቆየታቸውን ገልፀው ለዚሁ ወሳኝ ምዕራፍ ያደረሱትን ባለድተረሻ አመስግነዋል።
በክልሉ ምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ ተከስቶ የነበረው እና በሂደት ወደ ሌሎች እንዳይዛመት በርካታ ተግባራት እንደተሰሩ ያብራሩት የቆላማ አከባብዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት(LLRP) ስራ አስከያዥ አቶ ደረጀ በቀለ ለዚሁም በገንዘብ ድጋፍ ፈጣን ምላሽ ለሰጡት በተለይ የዓለም ጤና ደርጅትን አመስግነዋል።
የክልኩ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ የእንስሳት ጤና ዘርፍ ዳይረክተር ዶ/ር ብርሃኑ አለማየሁ ለዘመቻው አስፈላጊ የሰውና የቁስ ዝግጅት እንድሁም የተራጀ ቴክኒካል ቡድን መዘርጋቱን ገልፀው ከእንስሳት ክትባት ጎን ለጎን ከጤና ቢሮ ጋር ተቀናጅተን የሰዎችን ጤና ክትትል እያደረግን ነው ብለዋል።
እንስሳቶቻቸውን ለማስከተብ በማዕከሉ የተገኙ የአከባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው መንግስት እና ፕሮጀክቱ ለዝህ አስቸጋሪ እንስሳት በሽታ ፈጣን ምላሽ ስለሰጡ ምስጋናቸውን አቅርበው በየሰፈራቸው ተያይዘው አንድም እንስሳት ሰይቀር እንደሚያስከትቡ አስተያየታቸውን ሰተዋል።
በአሻግሬ ገ/ወልድ
