ቢስት ባር ወንድማማችነት እና የአብሮነት ጎልቶ የሚታይበት የቤንች ብሔር ታሪካዊና ባህላዊ ዕሴት አንዱና ዋነኛ ማሳያ ነው አሉ የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች።

Spread the love

ለቤንች ብሄር ዘመን መለወጫ (ቢስት ባር ) የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተጠናቀቀ ይገኛል።

የፊታችን ሰኞ ጀምሮ በድምቀት ለሚከበረው የቤንች ብሄር የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል (ቢስት ባር) የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በሚዛን አማን ከተማ እና በዓሉ በሚከበርበት የአማን የቀድሞ አየር ማረፊያ በልዩ ትኩረት እየተከናወነ ይገኛል።

የበዓሉን ዝግጀት ለማሳለጥ የተቋቋመው

ኮሚቴ የህብረተሰብ ተሳትፎ በማጠናከር ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የሚገልጹት የዝግጅት ኮሚቴ አባላት አሁን ላይ በዓሉ በዋናነት በሚከበርበት የቀድሞው አማን አየር ማረፊያ የመድረክ ዝግጅት እንዲሁም የበዓሉ ዕሴቶችን የሚያንጸባርቁ ዝግጅቶችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዚህም የመድረክ፣ የእንግዶች ማረፊያ ድንኳን ተከላ፣ መንገዶችን የማስዋብ ስራው በበዓሉ ኮሚቴ እና በአከባቢው ወጣቶች እየተከናወነ ይገኛል።

የበዓሉን መድረስ በጉጉት እንደሚጠበቁ የሚናገሩት የአከባቢው ነዋሪዎች ቢስት ባር ወንድማማችነት እና የአብሮነት ጎልቶ የሚታይበት የቤንች ብሔር ታሪካዊና ባህላዊ ዕሴት አንዱና ዋነኛ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህ የወንድማማችነትና የአብሮነት ማሳያ ቀን የሚመጥን ቅድመ ዝግጅት ለማድረግም የሚጠበቅ ዝግጅት ለማድረግ የበኩላችንን እየተወጣን በመሆናችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል

በከተማው የሚገኙ የንግድ ማዕከላት፣ የአግልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲሁም የህዝብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች የበዓሉን መድረስ በሚያበስሩ ባነሮች መድመቃቸውን መመልከት ችለናል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *