ትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ መጀመር የትምርት ቤት ደረጃን ለማሻሻል ዕድል እንደፈጠረላቸው የቴፒ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለድርሻ አካላት ተናገሩ።

Spread the love

ህብረተሰቡን በማሳተፍም የትምህርት ቤቱን ደረጃ ለማሻሻል ትኩረት በመስጠት እየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል ።

የቴፒ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የወላጅ ተማሪ መምህር ህብረት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጀማል ኢሳ የትምህርት ቤቱን ደረጃ ለመቀየር ህብረተሰቡን በማስተባበር እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል ።

በ1937 ዓ/ም እንደተመሠረተ የሚነገርለት ትምህርት ቤቱ የ80 ዓመት ቆይታውን ያህል እንዳልተለወጠ አቶ ጀማል ተናግረዋል ።

ቁጭትን ወደ ውጤት በመለወጥ ህብረተሰቡን ቀጥተኛ ተሳታፊ በማድረግ ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ በተሰራው ስራ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን እርምጃዎች ተጀምረዋል ብለዋል።

በዚህም ለትምህርት ቤቱ ባለ 4 ወለል ህንጻ ግንባታ ጅምር ስራዎች መኖራቸው ፣ በትምህርት ቤቱ አጥር ዙሪያ 25 ኮንቴይነሮችን በማሰራት ፣ ከህብረተሰቡ ሀብት በመሰብሰብ የትምህርት ቤቱን ደረጃ የማሻሻል ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በተገኘው ሀብት የአይሲቲ ቁሳቁስ ማሟላት፣ደረጃውን የጠበቀ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ፣ የተማሪዎች መቀመጫ ጥገናና ሌሎች ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ የሆኑ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።

በቀጣይም የትምህርት ቤቱን ደረጃ ለማሻሻል የተለያዩ ዕቅዶች ተነድፈው እንደሚሰሩም አብራርተዋል።

መምህር ዋሲሁን አዘነ በትምህርት ቤቱ የሂሳብ ሰራተኛ ሲሆኑ ከተለያዩ የገቢ ምንጮች በዓመት 3.5 ሚሊዮን ብር በመሰብሰብ የተለያዩ ስራዎች በትምህርት ቤቱ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በትምህረሰትቤቱ ደረጃውን የጠበቀ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመገንባትም ቁሳቁስ የማቅረብ ስራዎች ተጠናቅቀዋልም ብለዋል መምህር ዋሲሁን።

የትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር ሁሴን አሊ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መንገድ የመማር ማስተማር ስራ ውጤታማ እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ተማሪዎችን ውጤታማና ተወዳዳሪ ሆነው እንዲበቁ በተሰራው ስራ በትምህርት ዘመኑ 86 ከመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል መዛወር መቻላቸውንም መምህር ሁሴን ገልጸዋል።

የትምህርት ቤቱ ማህበረሰቦችም ለትምህር ቤቱ ደረጃ መሻሻል በጉልበት፣ በአይነትና፣ በክህሎቶቻቸው እንዲሁም በገንዘብ እየደገፉ እንደሚገኙና ይህንም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል ።

ትምህርት ቤቱ ባስገነባው ህንጻ ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ በመከራየት እየተገለገሉ ያሉ ግለሰቦችም ትምህረሰትቤቱ ገቢው እንዲያድግ እየተገለገሉበት ስለመሆኑም ተናግረዋል ።

በትምህርት ለትዉልድ መርሃ ግብር ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ዓመታት በካሽ፣ በዓይነት እና በጉልበት ከ1 በሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ ጥቅም ላይ መዋሉን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገልጿል፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊና የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ በረከት ኢዮብ እንደተናገሩት ህብረተሰቡንና ሌሎች አጋሮችን በማስተባበር ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብና በማስተባበር መጽሐፍት ታትሞ በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *