




የያዶታ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅና የያዶታ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ቀዶ ጥገና ማዕከል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል።
ኮሌጁ በ 66 ነጥብ 9 ሚለዮን ብር አዲስ ባስገነባው ህንጻ የአስተዳደር ክፍል፣የተማሪዎች መማሪያ ክፍሎች እና ቤተመጻሕፍት ክፍል የተካተተበት መሆኑ ታውቋል።
በሌላ በኩልም በክልሉ መንግስት ከ 11 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ የያዶታ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የቀዶ ጥገና ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል ።
በምረቃው ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የካፋ ዞን አመራሮች እንዲሁም የያዶታ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በታጠቅ አበበ
