




በስድስት ወራት ዉስጥ ብዙ ንጹህ መጠጥ ዉሃና የመስኖ ልማት ተቋማትን በማስመረቅ ለአገልግሎት ብቁ ማድረግ ተችሏል።
263.854 ኪ.ግራም ኪ/ግ ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ ገቢ ማድረግ መቻሉ፣
ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚውሉ 90ሺህ 180 ቶን የድንጋይ ከሰል ማምረት ተችሏል፡፡
ከሮያሊቲ ገቢ እና ከማዕድን ስራዎች 107ሚሊዮን 912ሺህ 300.86 ብር መሰብሰብ ተችሏል፡፡
በከተሞች መሠረተ-ልማት ግንባታ ነዋሪዉ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ተጠቃሚነቱን እንዲያረጋግጥ ከህብ/ሰቡ ከ81ሚሊዮን 331ሺህ ብር የሚገመት የገንዘብ፣ የጉልበትና ዓይነት በማሰባሰብ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል፡፡
በከተሞች የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ 3ሺህ164 መኖሪያ ቤቶች ፤ በገጠር የልማት ማዕከላት ደረጃቸዉ የተሻሻሉ 1ሺህ166 ቤቶችን መገንባት ተችሏል፡፡ 170 የመንግስት ቤቶች መረጃ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲደራጅ ታቅዶ 298 ቤቶች መረጃ በቴክኖሎጂ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡
በክልሉ እየተገነቡ ያሉ 3 መናኃሪያዎች አፈጻጸማቸው የቦንጋ 85% ፣ የታርጫ 96%፣ እንዲሁም የሚዛን 96% ማድረስ ተችሏል፡፡ ቀሪ ስራዎችን በማጠናቀቅ በቅርብ ጊዜ የሚመረቁ ይሆናል፡፡
17ሺህ 954 ተሽከርካሪዎች ላይ የትራፊክ ቁጥትር በማድረግ 942 አሽከርካሪዎች ከታሪፍ በላይ በማስከፈላቸው እርምጃ ተወስዶ በዚህም ለ12ሺህ 943 ተሳፋሪዎች 1ሚሊዮን 533,506 ብር ማስመለስ ተችሏል፡፡
በመንገድ ለመሠረተ ልማት ግንባታ የህብረተሰብ ተሳትፎና ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ 221ሚሊዮን 599ሺህ 384 ብር ማሰባሰብ ተችሏል፡፡
የአርብቶና ከፊል አርብቶ አደር ልጆችን በሆስቴሎች በድምሩ 179 ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ታቅዶ 172 ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡
በአርብቶ አደር አካባቢ የሚታየውን የተማረ የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ በሁለተኛ ዲግሪ 02፣ በመጀመሪያ ዲግሪ 90 እና በዲፕሎማ 18 ተማሪዎች ትምህርታቸውን በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡
በውሃ እና የመስኖ አውታር የጥናትና ዲዛይን እንዲሁም የግንባታ ሥራዎች በክልሉ መንግሥት የበጀት ድጋፍ መከናወናቸውን ርዕሰ መስተዳደሩ በሪፖርታቸዉ ጠቅሰዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
