የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ በታርጫ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

Spread the love

በጉባኤው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የመንግስታቸውን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የማህበራዊ ዘርፍ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለክልሉ ምክር ቤት እያቀረቡ ይገኛሉ።

👉ባለፉት ስድስት በትምህርት ዘርፍ ”ትምህርት ለትውልድ ኢንሼቲቭ” 372 ሚሊዮን 4መቶ 75 ሺህ በላይ ብር በመሰብሰብ 489 መማሪያ ክፍሎች ግንባታ፤ 1,385 መማሪያ ክፍሎች ጥገና ሥራ ማከናወን ተችሏል።

👉በክልል ደረጃ በልዩ ንቅናቄ 60 ትምህርት ቤቶች ግንባታ በማከናወን 27 ሞዴል ቅድመ አንደኛ ት/ቤቶች ተጠናቀዉ መማር ማስተማር ጀምሯል፤

👉የተማሪ – መጽሐፍት ጥምርታን ለማሻሻል የክልሉ መንግስት በበጀት 32 ሚሊየን ብር 131,796 ኮፒ የ7ኛና 8ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍት በማሳተም ጥምርታውን ከ1ለ7 ወደ 1ለ3 ማሻሻል ተችሏል፤

👉በክልሉ የአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እጥረት ለመቅረፍ 480 አዲስ ዲፕሎማ እና 251 ሰርተፊኬት ዕጩ መምህራን ስልጠና እንዲጀምሩ ተደርጓል፤

👉በጤና ዘርፍም የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ረገድ ምርመራ ከተደረገላቸው 1,087,550 ሰዎች ውስጥ 560,933 ሰዎች የወባ ተዋሲያን በደማቸው የተገኘባቸው ሲሆን አስፈላጊውን ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል፤

👉በክልሉ ከፍተኛ የወባ ጫና ባለባቸው 21 ወረዳዎች 662,158 የአልጋ አጎበር ለማህበረሰቡ ቤት ለቤት ማሰራጨት ተችሏል፤

👉የደም ባንክ አገልግሎት በተመለከተ በደም እጥረት ምክንያት የሚከሰተውን ህመም ስቃይና አላስፈላጊ ሪፈር ለማስቀረት 2830 ዩኒት ደም ማሰባሰብ ተችሏል፤

👉ከማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን 384 ሺህ 764 አዲስ አባላት በማፍራት የአባላት ምጣኔ ሽፋን 67.23% ማድረስ ተችሏል፤

👉ለማህበረሰብ ጤና መድን 417 ሚሊዮን 591 ሺህ 129 ብር መሰብሰብ መቻሉንና ባንክ ከገባዉ ገንዘብ 273 ሚሊዮን 122 ሺህ 295 ብር ወደ ጤና ተቋም ተላልፎ የመድሐኒት ግዥ ተፈጽሟል፤

👉የማህበረሰብ መድኃኒት ቤት ከ14 ወደ 28 ለማድረስ እየተሰራ ሲሆን በዚህ ግማሽ ዓመት አራት(በሚዛን ከተማ፥ ሲዝ ከተማ፥ ደብረ-ወርቅ ከተማ እና ሸኮ ከተማ) ተከፍቶ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ፤

👉በህገ ወጥ ምግብና መድሃኒት ላይ በተለያዩ ጤናና ጤና ነክ ተቋማት ላይ በተደረገ ቁጥጥር ግምቱ በአጠቃላይ በብር 3,047,055 በላይ የሚገመት ምርት ሊወገድ ተችሏል፣

👉የጤና መሰረተ ልማት አፈፃፀም የ2ኛው ትውልድ ጤና ኬላ ዳዉሮ ዞን የሚገኘዉ ቦሳሾጋ ሁለተኛ ትዉልድ ጤና ኬላ ግንባታ ፊዝካል አፈጻጸሙ 78% በላይ ማድረስ ተችሏል፣

👉የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ስራዎች አፈጻጸም በሚመለከት 660,616 ወጣቶች በክረምት እና በበጋ ወራት የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እንዲሳተፉ የተደረገ ሲሆን ይህም አገልግሎት በገንዘብ ሲተመን ብር 953,797,753 የሚገመት ነው፤

👉ከማህበራዊ ዘርፍ አኳያ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ 439 ነባርና አዲስ የድጋፍና እንክብካቤ ጥምረቶችን (CCC) ተገቢ ሚናቸውን እንዲወጡ መደገፍና ማጠናከር ተችሏል፣

👉የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ስራዎች አፈጻጸም በሚመለከት በቱሪዝም ዘርፍ የሀገር ውጭ ቱሪስቶችን ቁጥር 1961 እንዲሁም የአገር ውስጥ ጎብኝዎችን 1,146,715 እንዲደርስ ሥራዎች ተከናውኗል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *