




ከአንጻራዊነት ወደ ዘላቂነት እየተሸጋገረ ያለውን የክልሉን ሠላም ለማጽናት 225,174 የህብረተሰብ ክፍሎችን በሰላም፣ በብዝሃነት፣ በአብሮነትና በሰላም ግንባታ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር የአካባቢያቸውን ደህንነት በመጠበቅ ሰላምን በማረጋገጥ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ሥራ ተሰርቷል፤
58 የሰላም ምክር ቤቶችን በማጠናከር ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል፤
በሁሉም የወንጀል አይነቶች 4,081 መዝገቦች በዐቃቤያነ ህግ አስተያየት እና ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል፤
በኮሚሽኑ በመታረም ላይ ለሚገኙ 1340 ታራሚዎች ከ1ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል የቀለም ትምህርት እንዲያገኙ ተድርጓል፤
በሚዲያ መግለጫዎችም መንግስታዊ ሥራዎችን ለህዝብ ማድረስ በፕሬስ ሪሊዝም በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች የመንግስትን አቋም የማሳወቅ ሥራዎች ተከናዉኗል፣
የተለያዩ ሀገራዊና ክልላዊ ሚዲያዎችን በማስተባበርም ሰፊ የልማት ሥራዎች ከህዝቡ ጆሮና ዓይን እንዲገቡ በስፋት ተሰርቷል፤
የሚዲያና የህዝብ ግንኙነቱን ሥራ በአጀንዳ በመምራት፣ ብሔራዊና ክልላዊ ሁነቶች በታቀደላቸው መሠረት እንዲመሩ ተደርጓል።
የሪፎርም ሥራዎች ትግበራን ከማጠናከር አኳያ፤ በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዝግጅት ምዕራፍ ትግበራ ሰነድ በ 10 የፖሊሲ ማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች እና የፍኖቴ ካርታን ክልላዊ ይዘት ጠብቆ 1 ዙር ለማዘጋጀት ታቀዶ 1(100%) ተዘጋጅቷል።
በሰዉ ሃብት አመራር ልማት ዘርፍ ከመገንባት እና ከማብቃት አኳያ፤ የሰራተኞች ክልላዊ የሥራ መደብ ለማሻሻል 6806 ታቅዶ 3873 (57%) መታወቂያ ቁጥር ተሻሽሏል።
በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ስራ ሊመዘበር የነበረ እና በኦዲት ግኝት ክትትል ተደርጎ ብር 47,560,300 ማስመለስ ተችሏል፡፡ 1404 አዲስ የሀብት ምዝገባና ትክክለኛ ማረጋገጫ ማካሄድ ተችሏል፡፡
በፍቅር ከበደ
