




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዋ ሳፒ እንደገለፁት እያደገ የመጣውን የህዝብ የመሰረተ ልማት ፍላጎት ለማሟላት የጋራ ውይይት በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ ይገባል ብለዋል ።
በመሰረተ ልማት ክላስተር ሥር ያሉ ተቋማት በዕቅድ አፈፃፀም ያለውን ጥንካሬና ጉድለቶች በመለየት የጋራ አረዳድ በመያዝ ለቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም መዘጋጀት ይገባል ሲሉም አቶ ፋጂዋ ተናግረዋል።
ተቋማቱ የ9 ወራት አፈፃፀማቸውን እያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱ ላይ በጥልቀት ውይይት እንደሚካሄድበት ተጠቁሟል።
በሪፖርት ግምገማው የክልሉ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ፣ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ፣ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ እና አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ቢሮዎች ተሳትፈዋል።
