







የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት የክልሉ የአስተዳደር ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ3ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እየተገመገመ ይገኛል።
በግምገማዉ መድረኩ እንደክልል በሩብ ዓመቱ ታቅደው በጥንካሬ የተከናወኑ ተግባራት እንዲጠናከርና ድክመቶችን በጋራ በመገምገም እንዲሁም ቀጣይ ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ይደረጋል።
የክልሉ የአስተዳደር ተቋማት ማለትም ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ፣ የፍትህ ቢሮ፣ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ፣ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ፣ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት፣የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከነተጠሪ ተቋሞቻቸዉ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል።
በዚህም ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ የክልሉ የአስተዳደር ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በፍቅር ከበደ
