




የኢትዮዽያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከምርምር ማዕከላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው በተሻሻሉ የቡናና ቅመማቅመም ፓኬጆች ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና መድረክ በሚዛን አማን ከተማ ጀምረዋል።
መድረኩን ያስጀመሩት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አማካሪና የግብርና ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ መላኩ የኢትዮዽያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንን ለሀገራችን ኢኮኖሚ ፈር ቀዳጅ ለሆነው የቡናና ሻይ ዘርፍ ዙሪያ ስልጠና በክልላችን እንዲዘጋጅ ስላደረገ አመስግነዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያዊ ህዝቦች ክልል ቡና፣ሻይና ቅመማቅመም ባለስልጣን ዳይረክተር አቶ አስራት መኩርያ በበኩላቸው ስልጠናው እንደ ሀገር የዘርፉ ወሳኝ አከባቢን (strategic area) መሠረት ያደረገ ማለትም ምዕራብ ኦሮሚያን፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን እና ከጋምቤላ ክልልን የተወጣጡ አሰልጣኞችን ያካተተ መሆኑ ልዩ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
አቶ አስራት አክለው የክልላችን የተፈጥሮ ምህዳሩ ምቹ ከመሆኑም ባሻገር ቡናን ለዓለም ያስተዋወቀ እንድሁም ከ 1927 ዓ/ም ጀምሮ ሻይ ማምረት የጀመረ ብሆንም ከዘርፉ የተፈለገውን ያህል ምርት ካለማግኘት ቁጭት በመነሳት ከማሳ ልየታ እስከ ምርት ማሻሻል ድረስ ጠንክረን በመስራት ወደ ማዕከላዊ ገበያ 54,000 ቶን በላይ ቡና ፣ 50,000 ቶን ሻይ እና 6,654 ቶን ቅመማቅመም እያቀረብን ነው ብለዋል።
የስልጠናውን ይዘት ያብራሩት የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስጣን የቅመማቅመምና ሻይ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፈቃዱ ደፈርስ ከዝህ ቀደም የነበረንን ፓኬጅ ማሻሻያ (update) ለማድረግ ያለመ እና እንደየ አከባቢያችን ያለን ልምድ ልውውጥ የሚደረግበት ስልጠና እንደሆነ ተናግረዋል።
አቶ ፈቃዱ ጨምረው ፓኬጆችን ማሻሻል ያስፈለገው እንደ ሀገር የቡና መገኛ ቢንሆንም ከዘርፉ ተገቢ ምርት እየተገኘ ባለመሆኑና የ Export አቅማችንን ለማሳደግ እንድሁም ከቀድሞ የተሻለ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት መሆኑን ገልፀዋል።
በባለስልጣኑ የተዘጋጀው የተለያዩ የቅመማቅመም ምርቶች የሚያሳይ ኤግዝብሽን በሰልጣኞች ጉብኝት ከተደረገ በኃላ ከምርምር ማዕከላት በመጡ የዘርፉ ከፍተኛ ተመራማርዎች ስልጠናው መሰጠት ጀምሯል።
በአሻግሬ ገ/ወልድ
