በአዋጆቹ ዙሪያ የሚሰጠው ስልጠና ቀጥተኛ ያልሆነ ታክስን አሟጦ ለመሰብሰብ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው – ወ/ሮ ህይወት አሰግድ

Spread the love

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ የደንበኞች አገልግሎት የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ የስራ ክፍል ዘርፍ በክልሉ ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 34/2016፣ በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 36/2016 እንዲሁም በገጠር መሬት መጠቀሚያ ኪራይ እና የእርሻ ስራ ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 28/2016 ዙሪያ በዘርፉ ውስጥ ላሉ አዳዲስ ባለሙያዎች በሚዛን ከተማ ስልጠና እየሠጠ ነው።

በስልጠናው የቢሮው ምክትል ኃላፊና የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንዱ ታደሰ ክልሉ ሲመሠረት ከነበረበረበት ጊዜ አንስቶ ያለው የገቢ አሰባሰብ ሂደት ከፍተኛ ለውጥ የታየበት እንደሆነ ገልፀዋል።

በክልሉ ከሚመነጨው ኢኮኖሚ ገቢን አሟጦ ጠለመሰብሰብ እንዲቻል በተለይ አዲስ ወደ ተቋሙ የተቀላቀሉ ባለሙያዎችን በስራ ላይ የዋሉ አዋጆችና ደንቦች ላይ ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ይህ የስልጠና መድረክ መመቻቸቱን ተናግረዋል።

ስልጠናው ወደ ዘርፋ የተቀላቀሉ አዳዲስ ባለሙያዎች በቂ ግንዛቤ ይዘው ተግባራትን እንዲፈፅሙ በማስቻል ለብልሹ አሰራር ሳይዳረጉ ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብ ስለሚያስችል ሰልጣኞች ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው ስልጠናውን እንዲወስዱ አሳስበዋል።

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ የስልጠና መድረኩን በንግግር ሲያስጀምሩ እንዳሉት የክልሉ የገቢ ግብርና የታክስ አስተዳደር አዋጅ ክልሉ ከሚያመነጨው ኢኮኖሚ ግብርና ታክስ በፍትሃዊትና በአግባቡ አሟጦ ለመሠብሠብ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።

መንግስት በራሷ ገቢ የምትተዳደር ከእርዳታና ተመፅዋችነት የተላቀቀች ሀገር ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን አድርጓል ብለዋል።

በአዋጆቹ ዙሪያ የሚሰጠው ስልጠና በተለይ ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች የምናገኘውን ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው የገለፁት ኃሌፊዋ ገቢን በአግባቡ በስታንዳርድ መሠረት በፍትሃዊነት ለመሰብሰብም አይነተኛ ሚና እንዳለው አብራርተዋል።

ከስልጠናው ባሻገር በተግባራዊ ስራ እራሳችሁን በማብቃት ህግና ደንብን ተከትላችሁ ገቢን በየመዋቅሩ አሟጣችሁ መሰብሰብ አለባችሁ ሲሉ ወ/ሮ ህይወት ማሳሰባቸውን ከቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *