ከቡናው ዘርፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ቡና፣ሻይና ቅመም ባለስልጣን ከክልሉ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ በቡና ዕሴት ሰንሰለት ዙሪያ በተደረገ ጥናት ውጤት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በቦንጋ እየተካሄደ ይገኛል ።

መድረኩን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የክልሉ ቡና ፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ የመድረኩ ዓላማ በተለዋዋጭ ዓለም ውስጥ በቡናው ዕሴት ሰንሰለት ፤ በሚያጋጥሙ ጉዳዮች ላይ በየጊዜው የጋራ ምክክር ማድረግ ግንዛቤውን ለማሳደግ ያለመ እንደሆነ አንስተዋል።

አክለውም የባለድርሻ አካላት የቡና ዕሴት ሰንሰለት ላይ ከማሳ እስከ ግብይት ድረስ ያለው ሂደትን በተገቢው በመረዳት፣ የየድርሻቸውን ለመወጣትና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመለየት በጋራ በመፍታት ከዘርፉ የህብረተሰቡን ብሎም የክልሉን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መድረክ እንደሆነ አንስተዋል ።

በዘርፉ የሚገኙ ባለሙያዎችንና ባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ ከማሳደግም በላይ ተመራማሪዎች በቡና ዕሴት ሰንሰለት ውስጥ በማህበረሰብ አቀፍ የምርምር ስራው እንዲያግዙ ለማስቻል መድረኩ እንደሚያግዝ አቶ አስራት ጨምረው አብራርተዋል ።

በቡና ዕሴት ሰንሰለት ዙሪያ የዳሰሳ ጥናት ውጤት ሰነድ በዶ/ር ሀብታሙ ገ/ስላሴ ለተሳታፊዎች እየቀረበ ይገኛል።

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *