


የቢሮው ም/ሃላፊና የኢንቨስትመንት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ከበደ እንዳሉት ÷ በክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይበልጥ ለማነቃቃት በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
ባለፉት 5 ወራት 42 ባለሃብቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቁመው ÷ ወደ ሥራ ከገቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መካከል 34ቱ በግብርና ዘርፍ መሰማራታቸውን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም አምስቱ በአገልግሎት ዘርፍ እና ሦስቱ ደግሞ በኢንዱስትሪ ዘርፍ መሰማራታቸውን ነው ያስረዱት፡፡
በፕሮጀክቶቹ ከ35 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ እድልን መፍጠር መቻሉን አቶ ተስፋዬ አመላክተዋል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።
የክልሉን ሰፊ የመልማት አቅም ለመጠቀም በተከናወነ ሥራ የኢንቨስትመንት ፍሰት እየጨመረ መምጣቱን አስገንዝበዋል፡፡
በሁሉም የኢንቨስትመንት ዘርፎች ክልሉን ለማልማት ከባለሃብቱ ጋር በትብብር እንደሚሰራ ጠቅሰው ÷ በተለይም በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሚሰማሩ አልሚዎች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
