የመረጃ ተደራሽነቱን ለማስፋት የታየው ቅንጅታዊ አሰራር አበረታች መሆኑ ተገለጸ

Spread the love

ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተውጣጣ የድጋፋዊ ክትትል ቡድን በክልሉ በሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ላይ ድጋፍዊ ክትትል አድርገዋል ።

በዚህም በቅርብ ጊዜ በይፋ ተመርቆ አገልግሎት ለህብረተሰቡ እየሠጠ የሚገኘው የቤንች ሸኮ የማህበረሰብ ቴሌቪዥን አንዱ ነው ።

ምንም እንኳን በቅርብ ጊዜ ተቋሙ የተደራጀ ቢሆንም የመረጃ ተደራሽነትን ሁሉ አቀፍ ለማድረግ የተጀመሩ ቅንጅታዊ አሰራሮች አበረታች እንደሆነ በመስክ ምልከታው ወቅት የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የህዝብና የሚዲያ ግንኙነት ዳይሮክተሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ በረከት ተናግረዋል ።

የድጋፍ ቡድኑ የቤንች ሸኮ የማህበረሰብ ቴሌቪዥን ይዞ ከተነሳው ዓላማ አንጻርም አደረጃጀቱ ፣ የአሰራር ስርዓቱን ተዘዋውረው ተመልክተዋል ።

ቴሌቪዥን ጣቢያው በተለይ በማህበራዊ ድረ ገጸቹ የሚለጠፉ ዘገባዎች በአጭር ጊዜ በርካታ ተከታይ ማፍራት መቻሉ በየደረጃው ከሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ጋር የታየው መቀናጀት የሚበረታታ ተግባር እንደሆነ ነው ወ/ሮ በረከት የገለጸት ።

አንደ ወ/ሮ በረከት ገለጸ በተቋሙ ገበያ ለመፍጠር የተጀመሩ ሰራዎች የይዘት ጥራት ውጤት በመሆናቸው አጠናክሮ መስራት ይገባል ብለዋል ።

በአነስተኛ የሰው ሀይል ውጤታማነትን ያሳዩ ተቋም መሆኑንም የድጋፍ ቡድኑ አንስቷል ።

ቴሌቪዥን ጣቢያው በዞኑ በአጭር ጊዜ ተመሠርቶ የዞኑን ብሎም የክልሉን ህዝብ ሁሉ አቀፍ በሆኑ መረጃዎች ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ የተናገሩት የቤንች ሸኮ ዞን የኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በላቸው ጎንደር ናቸው።

የዞኑን የዘገባ ሸፋን በማሳደግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም አቶ በላቸው አስረድተዋል።

ከቡድኑ የተቋሙ ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ አሰፋ በቀጣይ የበለጠ ለመስራት የሚያስችል ጠቃሚ አስተያየት በመሰጠቱ አመስግነው የሌሎች ተቋማት ተሞክሮም በመውሠድ በማሰፋት አንደሚሠራ ገልጸዋል።

ለተቋሙ የበለጠ ውጤታማነት የተገልጋዩን ማህበረሰብ ፍላጎት መሠረት በማድረግ የተጀመሩ ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም የድጋፍ ቡድን አባላትም ማሳሰባቸዉን የቤንች ሸኮ ቴቪ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *