በተሻሻለው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 03/2017 ላይ እና በዳኞች ሥነ- ምግባር ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳውሮ ዞን ከፍተኛ፣ የወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ለተወጣጡ ዳኞች በተሻሻለው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በታርጫ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የዳውሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት አቶ አሮታ አልባዞ እንደገለፁት የስልጠናው ዓላማ የዳኝነት አካሉን ግልፅነት እና ተጠያቂነት ባረጋገጠ መልኩ ውጤታማ እና ተገማችነት ያለው ቅጣት የሚወሰንበት ሥርዓት መመሥረት ነው።

እንዲሁም ሥልጠናው አሁን በተሻሻለው በአዲሱ መመሪያ ቁጥር 03/2017 ዙሪያ ለሰልጣኞች በቂ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ በመሆኑ በተገቢው እንዲከታታሉ አሳስበዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት ዳኛ አቶ ናስር አቡዱ ለስልጠና የተዘጋጀውን ሰነድ በሚያቀርቡበት ወቅት እንደተናገሩት የሰልጠናው ዋና ዓላማ ተቀራራቢ እና ተመሣሣይነት የወንጀል ጉዳዮች መካከል ተቀራራቢነት ያለው ቅጣት እንዲወሰን ማድረግ ነው።

የተሻሻለው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ 03/2017 ከዚህ ቀደም በነበረ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ 02/2006 ላይ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ሊያርም እንደሚችል ገልፀዋል ።

ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መምሪያ ቁጥር 03/2017 ላይ እና በዳኞች ሥነ- ምግባር ዙርያ የሚያጠነጥን እንደሆነ ከወጣው መረሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል ሲል የዳዉሮ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ነው ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *