




47 አነስተኛና መካከለኛ አዳዲስ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ዘርፉ እንዲቀላቀሉ በማድረግ ለዜጎች የስራ ዕድል እንዲፈጠር ማድረግ ተችሏል፡፡
አዲስ ፍቃድ ከሚወስዱ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች 2ሚሊዮን 271ሺህ 890,371 ካፒታል ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
በሥራ ላይ ከሚገኙ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች 28ሺህ 398 ዜጎች በቋሚ መፍጠር ተችሏል፡፡
በኦዲት ከተገኘዉ ግኝት ወደ መንግስት ቋት 55ሚሊዮን 435ሺህ 167 ገቢ ተደርጓል፡፡
የክልሉ ጠቅላላ ገቢ በግማሽ አመቱ ብር 8 ቢሊዮን 358ሺህ 681,528.37 የዕቅዱ (90.76%) መሰብሰብ ተችሏል።
በክልላችን ያጋጠመዉን የፋይናንስ ጉድለት መነሻ በማድረግ የሰብአዊ አገልግሎቶች ግዴታ ወጪዎች ለመሸፈን ከፌዴራል መንግስትና ከተለያዩ ምንጮች በብድር የተወሰደ የጥሬ ገንዘብ ብር 292.1 ሚሊዮን፣ የግብዓት ዕዳ ብር 96.9 ሚሊዮን፣ የጡረታ ማህበራዊ ዋስትና ያልተከፈለ ዕዳ ብር 111.2 ሚሊዮን በድምሩ 500.2 ሚሊየን ብር መመለስ ተችሏል፡፡
የመንግስታት ትብብር እና ሲቪል ማህበረስብ ዘርፍ በሚመለከት የዉጭና ሀገር በቀል ሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ኘሮጀክቶች ስታንዳርዱን የጠበቀ የአጋማሽና የማጠቃለያ ጊዜ ግምገማ ለማካሄድ 15 ታቅዶ 15 የተከናወነ ሲሆን በበጀት ብር 1.422 ቢሊየን ለመፈራረም ተችሏል፡፡
1500 ዜጎችን ወደ ዉጪ ሀገር ለሥራ እንድሰማሩ ማድረግ ተችሏል፡፡
በስድስት ወራት ለ24 ሺህ 463 ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡
በዕድገቱ በዛብህ
