ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ ለክልሉ ምክር ቤት የመንግስታቸዉን የ2018 በጀት ዓመት ግማሽ ዓመት ሪፖርት እያቀረቡ ይገኛሉ።

Spread the love

በርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ በክልሉ ምክር ቤት ከቀረበው የኢኮኖሚ ዘርፍ ሥራዎች አፈጻጸም÷

👉በ2017/18 ምርት ዘመን በመኸር በዋና ዋና የአዝርዕት ሰብሎች 384ሺህ 160 ሄ/ር ማሳ በዘር ተሸፍኗል፡፡

👉ባለፈው በልግ ከተሸጋገረዉ ማሳ 20,327,613 ኩ/ል ምርት ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡

👉 85 ሺህ 568 ሄ/ር በመኸር ወቅት የኩታ ገጠም እርሻ በዋና ዋና አዝዕርት ሰብሎች ተሸፍኗል፡፡

👉5ሺህ 585 ሄ/ር ማሳ ለበጋ የመስኖ ስንዴ ማሳ ተዘጋጀቷል፡፡

👉119ሺህ 905 ኩ/ል የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ሥርጭት

👉214 ሚሊዮን 707ሺህ 382 የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በመትከል 66ሺህ 347 ሄ/ር መሬት ተሸፍኗል፡፡

👉60ሺህ 504 የ2ኛ ደረጃ የመሬት ልኬትና ምዝገባ በማድረግ ለ14ሺህ 030 ባለይዞታዎች ይዞታ ማረጋገጫ ደብተርና ሰርተፍኬት ሥርጭት ተደርጓል፡፡

👉1ሚሊዮን 247ሺህ 326 ቄብና ኮክኔ በማሰራጨት 147.13 ሚሊዮን እንቁላል ተመርቷል፡፡

👉987 የማር መንደር በማደራጀት 14ሺህ 138 ዘመናዊ ቀፎ ማሰራጨት የተቻለ ሲሆን 14ሺህ 851 ቶን ማር ማምረት ትችሏል፡፡

👉4ሺህ 904.25 ቶን ዓሳ ከተለያዩ ዉሃ አማራጮች በማምረት ለገበያ ማቅረብ ተችሏል፡፡

👉3,340,868 ኩንታል የቅመማ ቅመም ምርት መሰብሰቡን፣

👉104ሺህ 986ቶን እሸት ቡና በማዘጋጃ እንዱስትሪዎች እንድቀርብ ተደርጓል፡፡

👉13ሺህ 181 ቶን የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል፡፡

👉 2ሺህ 707 የሻይ ምርት ለሀገር ዉስጥና ለዉጪ ገበያ ማቅረብ ተችሏል፡፡

👉3ሚሊዮን 783ሺህ 440 ከደን ውጤቶች የሮያሊት ክፍያ ገንዘብ መሰብሰብ ችሏል፡፡

👉37ሺህ 633 የንግድ ስራ ፈቃድ ዕድሳት እንዲሁም 7ሺህ 160 አዲስ የንግድ ምዝገባ ለመመዝገብ መከናዉኑን፡፡

👉በስድስት ወራት 32 ሚሊዮን 043ሺህ 409 ሊትር ናፍጣ እና 6ሚሊዮን 488ሺህ 880ሊትር ቤንዚን ቀርቦ ተሰራጭቷል፡፡

👉በህገ-ወጥና በኮንትሮባንድ የንግድ እንቅስቃሴ 23ሚሊዮን 045ሺህ 109 ብር የሚገመት ምርት ተይዞ ለመንግስት ገቢ ተደርጓል፡፡

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *