ለረዥም ዓመታት የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የነበሩ ሁለት የድልድይ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ተመረቁ።

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፥ በቤንች ሸኮ ዞን የተገነቡ የአጉና እና የዳማ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቀው ለአግልግሎት ክፍት ሆነዋል።

በክልሉ መንገዶች ባለስልጣን መስሪያ ቤት አሰሪነት ተገንብተው የተመረቁት እኚሁ ፕሮጀክቶች ለሁለቱ ድልድዮች መደረሻ መንገድ ግንባታ ስራ ማስፈፀሚያን ጨምሮ ጠቅላላ 47 ሚሊዮን 3 መቶ ሺህ ገደማ ብር ወጪ እንደወጣበትም ነው የባለሥልጣን መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር አብድዩ መኮንን የገለጹት።

የአጉ ወንዝ ድልድይ በአማን-ጋሪቅን የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ላይ የተገባ ሲሆን የሚዛን አማን ከተማ የኮመታ ቀበሌንና ከሸኮ ወረዳ ፋጅቃ ቀበሌን ከሚዛን አማን ከተማ ጋር በቀጥታ ከማገኛነቱም በተጨማሪ በቀበሌዎቹ ዉስጥ ስራ ያሉ የቺፒዉድ ፋብርካ እና የቡና መፈልፈያ ኢንዱስትሪዎች የዕለትለት እንቅስቃሴዎች በማሰለጥ ጉልህ ሚና ያለዉ ፕሮጀክት መሆኑ ነው የተገለጸው።

በሌላ በኩል በዳማ ወንዝ የተጣለው ድልድይ በዞኑ የጊድ ቤንች እና ሰሜን ቤንች አከባቢዎች እርስበርስ ከማስተሳሰርም በላይ የጊድ ቤንች ወረዳን ከዞን ማዕከል ጋር በሚያገኛን እንደኬል-ዲዙ መንገድ ላይ የተገባ መሆኑንም ነው ኢንጂነር አብድዩ የገለጹት።

በ2011 እና 2012 በቀድመው ክልል ተጀምረው ግንባታቸው የተጓተተው እኚሁ የድልድይ ግንባታ ፕሮጀክቶች በአከባቢው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆነው ስነሱ የነበሩት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መመሥረት በኃላ የክልሉ መንግሥት በሰጠው ልዩ ትኩረት መጠናቀቁ ነው የተገለጸው።

በምረቃው ስነስርዓት የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞን ጨምሮ የክልል እና የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *